የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኞቹ ከ44 ቀን እስር በኃላ በዋስ እንዲፈቱ አዟል
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኞቹ ከ44 ቀን እስር በኃላ በዋስ እንዲፈቱ አዟል
ላለፉት ቀናት በእሥር ላይ የነበሩት የአሥራት ሚዲያ ሀውስ ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ባስያዙት ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ሲል ፍርድ ቤት መወሰኑ ተገለጸ፡፡ የአሥራት ባልደረቦች በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ቀደም ሲል በዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ከእሥር ሳይወጡ መቆታቸው ይታወሳል፡፡
በመቀጠልም ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን ከእሥር እንዲለቀቁ መወሰኑን የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች ለአል ዐይን ገልጸዋል፡፡
የልደታ ፍ/ቤትየፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንዲወጡ አዟል፡፡ ዛሬ በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ምንም አዲስ ነገር ያገኘው እንደሌለ ገልጾ ጋዜጠኞቹ በነፃ እንዲወጡ ትዕዝዛ ሰጥቷል።
ከአርቲስቱ ግድያ በኃላ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል 239 ሰዎች በላይ መሞታቸውን መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡