“ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው ሮናልዶ በዩትዩብ የሰበራቸው አዳደስ ክብረ ወሰኖች?
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዩትዩብ ገጽ በከፈተ በሰአታት ውስጥ ከፍተኛ ክፍያ ማግኝት ጀምሯል
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ የተከፈተው የዩቱብ ቻናሉ 8 አዳዲስ ክብረ ወሰኖችን ሰብሯል
`ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዩትዩብ የሰበራቸው አዳደስ ክብረ ወሰኖች መስበሩን ቀጥሏል።
የ39 አመቱ የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዩትዩብ ገጽ በከፈተ በሰአታት ውስጥ ከፍተኛ ገቢ ማግኝት መጀመሩ ተነገረ፡፡
በሳኡዲ ሊግ ለአል ናስር እየተጫወተ የሚገኝው ሮናልዶ በስፖንሰር ሺፕ እና በፊርማ ክፍያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ ስፖርተኞች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡
በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገጽ 636 ሚሊየን ተከታዮችን በማግኝት ከአለም ቀዳሚው የሆነው ሮናልዶ ከትላንት በስቲያ በከፈተው የዩትዩብ ገጽም ክብረ ወሰኖችን እየሰባበረ ይገኛል፡፡
“ዩአር” ክርስቲያኖ በሚል ስያሜ የከፈተው ዩትዩብ 90 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ ተከታዮችን የሰበሰበ ሲሆን በአሁኑ ወቀት 30 ሚሊየን ሰብስክራይበሮችን አግኝቷል፡፡
ከ 4 ደቂቃ ያልበለጡ 19 አጫጭር ቪድዮዎችን የለቀቀው ክርስቲያኖ እስካሁን ከ3.1 እሰከ 24 ሚሊየን ድረስ እያንዳንዱ ቪድዮዎቹ ታይተውለታል፡፡
የዩትዩብ ገጽ ባለቤቶች አንድ ቪድዮ ለሚያገኝው አንድ ሺህ እይታ ከ2 –12 ዶላር ያገኛሉ ዩትዩብ ከማስታወቂያ ክፍያ የሚያገኝውን ገቢ 45 በመቶውን በመውሰድ 55 በመቶውን ለገጹ ባለቤቶች ይሰጣል፡፡
የሮናልዶ ገጽ አጠቃላይ የቪድዮ እይታ በአሁኑ ወቅት ከ120 ሚሊየን በላይ ተሻግሯል፡፡
በሰአታት ውስጥ በከፈተው ገጽ ከፍተኛ ሚሊየን ተከታዮችን ማግኝት የቻለው ሮናልዶ አሁን ላይ በዩትዩብ ከፍተኛ ተከታዮችን በመያዝ ቀዳሚ ከሆነው “ሚስተር ቢስት” ጋር ሊፎካከር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
የተለያዩ የመዝናኛ እና የውድድር ይዘቶችን በመስራት የሚታወቀው ሚስተር ቢስት 400 ሚሊየን እይታን በማግኝት በወር 5 ሚሊየን ዶላር ከዩትዩብ ይከፈለዋል፡፡
ክርስቲያኖ የዩትዩብ ገጹን ከአለም አቀፍ አድናቂዮቹ ጋር ይበልጥ ለመቀራረብ እንደሚጠቀምበት አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም እስከዛሬ ሰዎች ያላዩትን የግል ህይወቱን ክፍል በገጹ እንደሚያጋራ እና የተለያዩ እንግዶችን በማቅረብ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ማቀዱን ነው የገለጸው፡፡