አይኤምኤፍ ብድር ለመስጠት የሚጠቀማቸው መስፈርቶች
አይኤምኤፍ የሀገራትን ፋይናንስ የማስተዳደር አቅም ይገመግማል
አይኤምኤፍ ብደር ለለመስጠት ሀገራት ፖሊሲ ለማሻሻል ያላቸውን ፍቃደኝነት ያያል
አይኤምኤፍ ብድር ለመስጠት የሚጠቀማቸው መስፈርቶች
አለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ለሀገራት ብድር ለመስጠት በርካታ መስፈርቶችን ይጠቀማል።
1) የኢኮኖሚ ፖሊሲ፦
የሀገራትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመገምገም ዘላቂ እና የተረጋጋ ልማት መኖሩን ያረጋግጣል
2) ፊሲካል ዘላቂነት
የሀገራትን ፋይናንስ የማስተዳደር አቅም ይገመግማል
3) ሪፎርም እና የመዋቅር ለውጥ
ሀገራት የኢኮኖሚ አለመጣጠን ችግሮችን ለመፍታት ማሻሻያዎችን ለማድረግ ያላቸውን ፈቃደኝነት ያያል
4) ባላንስ ኦፍ ፔይመንት
አይኤፍ ሀገራት አለምአቀፍ የፋይናንስ ግዴታዎችን የማሟላት አቅማቸውን እና የተረጋጋ ገንዘብ መኖሩን ይመረምራል።
5) የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት
አይኤምኤፍ የኑሮ ውድነት ደረጃን፣ የምንዛሬ ምጥነትን እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ጤናማነትን ይገመግማል።
6) የእዳ ደረጃ
አይኤምኤፍ ሀገራት ያለባቸውን የእዳ ጫና በማየት ተጨማሪ እዳ ቢበደሩ መረጋጋት ይኖራል ወይ የሚለውን ይገመግማል
7) ተቀማጭ ገንዘብ እና የፋይናንስ ጤንነት
አይኤምኤፍ በቂ ተቀማጭ ገንዘብ እና ጤናማ የፋይናንስ ስርአት መኖሩን ከግምት ያስገባል
አይኤምኤፍ እነዚህን መስፈርቶች ሀገራት መበደር ይችላል ወይስ አይችሉም የሚለውን ለመወሰን ይጠቀምባቸዋል።