ስቅለትን ልክ እንደ ኢየሱስ ክርቶስ በመስቀል ላይ በመቸንከር የሚያከብሩት ፊሊፒናውያን
ስምንት ፊሊፒናውያን በስቅለተ ክርስቶስ አምሳል በሚስማር ተቸንክረው ተሰቅለዋል
ስቅለተ ክርስቶስ አምሳል ለ34ኛ ጊዜ የተሰቀለ ግለሰብ አለ
በፊሊፒንስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው ስቅለተ ክርስቶስ አምሳል ዳግም መከበር ተጀምሯል።
በፊሊፒንስ ማዕከላዊው የፓምፓንጋ ግዛት ውስጥ በሚከበረው ለየት ባለው የስቅለት በዓል ላይ ፊሊፒናውያኑ ራሳቸውን በኢየሱስ ክርቶስ አምሳል መስቀል ላይ መቸንከራቸው ተነግሯል።
በዚህም የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ተመስሎ ለማሳየትም ስምንት ፊሊፒናውያን፣ ከእንጨት በተሰራ መስቀል ላይ በሚስማር ተቸንክረው መሰቀላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ግለሰቦቹ 10 ሴንቲ ሜትር በሚረዝም ሚስማር እግራቸው እና እጃቸው በዕንጨት ላይ ከተቸነከረ በኋላ ለ10 ደቂቃ ወይም ከዚያም በላይ በእንጨት መስቀሉ ላይ መቆታቸውም ተነግሯል።
ለ34 ጊዜ በመስቀል ላይ የተቸነከረው የ62 አመቱ ሩበን ኢናጄ፤ በዚህ ተግባር ላይ ደስተኛ መሆኑን እና ሁልጊዜ በመሰቀል ላይ ስቸነከር ክቅሚያ ጸሎት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ኢናጄ፤ 10 ሴንቲሜትር በሚረዝም ሚስማር በእጁ እና እግሩ ላይ የተቸነከረ ሲሆን፤ ሚዛል ለመጠበቅ ሲባል ደግሞ በግራ እና በቀኝ በኩል በገመድ መታሰሩም ታውቋል።
ስቅለተ ክርስቶስ አምሳል ተግባር ላይ ሰዎች ከፈረንጆቹ 1955 ጀምሮ ሲሳተፉ መቆየታቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪ አስታውቋል።
ፊሊፒንስ ካላት 94 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ 80 በመቶው የካቶሊክ ምነት ተከታዮች ሲሆን፤ የካቶሊክ ቤት ክርስቲያን ግን ስቅለተ ክርስቶስ አምሳል ተግባርን አትብቃ ትቃወማለች።