የትግራይ አባቶች የቤተክርስቲያኗን ማሳሰቢያ በመተው ኤጲስ ቆጾሳትን መረጡ
ቤተክርስቲያኗ ይህን የትግራይ አባቶች እንቅስቃሴ እንዲያስቆም መንግስትንም ጠይቃ ነበር
በትግራይ አባቶች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ የትግራይ አባቶች ቤተክርስቲያኗ ጦርነት አላወገዘችም በሚል ነበር
የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የትግራይ አባቶች ኤጲስ ቆጾሳትን የመሾም እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ አሳስባ ነበር።
ቤተክርስቲያኗ ይህን የትግራይ አባቶች እንቅስቃሴ እንዲያስቆም መንግስትንም ጠይቃ ነበር
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀች
- ቤተክርስቲያኗ ጠ/ሚንስትር አብይና አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ይካሄዳል የተባለውን የኤጲስ ቆጰሳት ሹመት እንዲያስቆሙ ጠየቀች
ነገርግን የትግራይ አባቶች የቤተክርስቲያኗን ማሳሰበያ ወደጎን በመተው በዛሬዎ እለት በአክሱም ለሀገር ውስጥ አምስት እና ለውጭ አምስት በድምሩ 10 ኤጲስ ቆጾሳት መምረጣቸውን መስጠታቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በትግራይ አባቶች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ የትግራይ አባቶች ቤተክርስቲያኗ ጦርነት አላወገዘችም በሚል ነበር።
ቅሬታ ያነሱት አባቶችም "የትግራይ መንበረ ሰላማ ቤተክህነት" ማቋቋማቸው እና ከቤተክርስቲያኗ አደረጃጀት መውጣታቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ቤተክርስቲያኗ ከትግራይ አባቶች ጋር ያለውን አለመግባባት በውይይት ለመፍታት ጥረት ማድረጓ ይታወሳል።
የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰኔ 28፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ህዝበ ትግራይን ይቅርታ ጠይቃ ችግሩን በውይይት ለመፍታት የሉኡክ ቡድን ወደ መቀሌ መላኳ ይታወሳል።
ይሁን እንጅ የቤተክርስቲያኗ ልኡክ በመቀሌ ከትግራይ አባቶች ጋር ሊያደርግ የነበረው ውይይት አለመሳካቱን እና ይህም እንዳሳዘናት ገልጻ ነበር።
በቤክርስቲያኗ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ እና መፈንቅለ ሲኖዶስ ስትል የጠራችው ችግር የተከሰተው ባለፈው ጥር ወር ሶስት አባቶች ከቀኖና ውጭ 25 ኤጲስ ቆጾሳትን መሾማቸውን ተከትሎ ነበር።
ጥር 14፣2014 ዓ.ም በደቡብ ምእራብ ሽዋ ሀገረስብከት ከቀኖና እና ህገቤተክርስቲያን ውጭ የሾሙት እና የተሾሙት አባቶች ተወግዘው ከቤተክርስቲያን እንዲገለሉም መረጋቸው ይታወሳል።
ነገርግን በተደረጉ ወይይቶች አባቶች ላይ የተጣለው ውግዘት እንዲነሳላቸው እና ተጨማሪ ኤጲስ ቆጾሳት እንዲሾሙ ስምምነት መደረጉን እና ቤተክርስቲያኗም ችግሩን በቀኖኗዋ መሰረት መፍታቷን ገልጻ ነበር።
በዚህ መሰረት ቤተክርስቲያኗ በዛሬው እለት ጠዋት "ችግር ላለባቸው አካባቢዎች" ዘጠኝ ኤጲስ ቆጾሳትን በመንበረ ፖትሪያርክ ቅድስ ማሪያም ገዳም በተካሄደ ስነስርአት ሲመት ሰጥታለች።
በዛሬው እለት የኤጲስ ቆጾሳት ለመምረጥ አቅድው የነበሩት ትግራይ አባቶች ምርጫውን ማከናወናቸው ከቤተክርስቲያኗ ጋር ያላቸውን አመግባባት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አድርሶታል።