አቶ ደመቀ ህወሓት ለጥፋት ዓላማ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳያልፉ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ
በአፋር ክልል ከ1 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ
አቶ ደመቀ በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው የሰብዓዊ ድጋፎችን ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ተመልክተዋል
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለጥፋት ዓላማ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች ለህወሓት እንዳይተላለፉ አሳሰቡ፡፡
አቶ ደመቀ በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው የሰብዓዊ ድጋፎችን ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ከሌሎች የፌዴራል እና የክልሉ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ ደመቀ የአፋር ህዝብ በህወሓት ወረራ ምክንያት ከ1 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮችን ይዞ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ ለሚገኘው ጥረት ያሳየውን ቀና ትብብር አድንቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጦርነት የገቡ አካላትን ለማስታረቅ ጠየቀች
በየደረጃው ያሉትን የክልሉን ነዋሪዎች ያመሰገኑም ሲሆን ሰብዓዊ እርዳታዎችን በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ወደተጎዱ ወገኖች ለማድረስ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፤ ከዚህም ውስጥ ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አንዱ መሆኑን በመጠቆም፡፡
በሰርዶ ኬላ ተገቢው የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ በቀን እስከ 200 ኮንቮይ ተሽከርካሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ እንደሚያቀኑም ተናግረዋል አቶ ደመቀ፡፡
ይሁንና በተደረገዉ ፍተሻ ለሽብር ቡድኑ የጥፋት አላማ ማስፈጸሚያ ሊውሉ የሚችሉ ከተፈቀደው የነዳጅ መጠን በላይ ተጨማሪ ነዳጅና አንዳንድ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ለማሳለፍ ሙከራዎች አንዳሉ መገንዘባቸውን ነው የተናገሩት፡፡
መሰል ተግባራት ከሰብዓዊ አቅርቦት ህጉ የሚጣረሱ በመሆኑ ከሚመለከታቸው ሰብዓዊ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር መንግስት ይነጋገርበታልም ብለዋል፡፡
በመሆኑም እርዳታዎችን ትግራይ ለማድረስ ከሚደረጉ ጥረቶች ጎን ለጎን ህወሓት ለጥፋት ዓላማው ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰባቸውን ኤፍ.ቢ.ሲ ዘግቧል።