የዲሞክራሲ ዘመን እያበቃ ይሆን?
ለረጅም ጊዜ ዲሞክራሲ ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለህዘባዊ ውክል ቦታ የሚሰጥ የመንግስት አስተዳደደር ተደርጎ የሚታይ ነው
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዲሞክራሲ ስርአት ሚና የሚቀንስበት ዘመን ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል
ለረጅም ጊዜ ዲሞክራሲ ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለህዘባዊ ውክል ቦታ የሚ ሰጥ የመንግስት አስተዳደደር ተደርጎ የሚታይ ነው።
ዲሞክራሲ ዘመናዊ ማህበረሰብ እንዲፈጠር እና የግለሰብ መብት እንዲከበር አይነተኛ ሚና መጫወቱ እሙን ነው። ነገርግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዲሞክራሲ ስርአት ሚና የሚቀንስበት ዘን ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ መጥቷል።
የመቀነሱ ምልክቶች በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም። በመላው አለም የህዝባዊ(ፖፑሊስት) መሪዎች መጨመርን እና የዲሞክራሲ እሴቶ ች እና ተቋማት ሲሸረሸሩ እያየን ነው። ህዝብ ባለበት ችግር ላይ የሚያተኩሩ እና የተፈጠሩ ክፍፍሎችን የሚጠቀፖ ፑሊስት መሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ እያገኙ ናቸው። እነዚህ መሪዎች ሁልጊዜ ይዘውት የሚመጡት ትርክት የአካታችነት ፣ ለጥቶ መቀበል ፖለቲካ እና ለዲሞክራሲዊ ሂደት የሚመች አይደለም።
በማህበረሰቦች መካከል እየጨመረ የመጣው ቅራኔ(ፖላራይዜሽን) ለችግሩ በዋ ናነት አስተዋጽኦ ያደርጋል። የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ከፋፋይ እና ለገንቢ ንግግር እና የጋራ መፍትሄ ላ ይ ለመድረስ የማይመቹ ይሆናሉ።
ቅራነው ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ሀሳቦች እንዲፈጠሩ የሚያደርግ ሲሆን ይህ የዲ ሞክራሲ እሴቶችን ይሸረሽራል።
የዲሞክራሲ ተቋማማት መሸርሸር ከንዱ የስጋት ምንጭ ነው። የህግ ተርጓሚ ነጻነት፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የቁጥጥር ተቋማት ገለልተኛት የጤናማ ዲሞክራሲ ወሳኝ መገለጫዎች ናቸው። ነገርግን እነዚህ ተቋማት ህግ አሰፈጻሚዉን እንዳይቆጣጠሩ ዛቻ እና ጣልቃ ገብነት ሲገጥማቸው እያናያለን።
ከዚህ በተጨማሪ ገንዘብ በፖለቲካው ውስጥ ያለው ተጽእኖ እና የስልጣን ጥቅመኞች መኖር በዲሞክራሲ ስርአት ላይ አደጋ ደቅነዋል። ገንዘብ የፖለቲካ ውሳኔዎችን ሲያስቀይር፣ የተራ ዜጎች ድምጽ አይሰማማም፣ በዲሞክራሲ ላይ የነበረው እምነትም ይጠፋል።
ዲሞክራሲ የተጋረጠበትን ችግር በማወቅ፣ የዲሞክራሲ እሴቶችን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች፣ የሚዲያ ተቋማት እና ዜጎች መንግስት ተጠያቂ እንዲሆን እና ዲሞክራሲያዊ ማሻሻያዎች እንዲኖሩ መስራት ይጠበቅባቸዋል።
ዲሞክራሲን ጠብቆ ለማቆየት ግልጸኝነትን መጠናከር፣ የሲቪክ ትምህርትን ማስፋፋት እና አሳታፊ ፖለቲካን ማራመድ ዲሞክራሲን ለማራመድ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።
በአጠቃላይ የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመጠበቅ እና ችግሮቹን ለመቅረፍ የጋራ ጥረት ያስፈልጋል።