500 ዓመታትን ያስቆጠረው እና በዓለት ላይ የተመሰረተው የየመን መንደር
ለጥንታዊ ቤቶቹ ግንባታ ጭቃ እና ገለባ ጥቅም ላይ መዋላቸው ባለሙያዎች ይገልጻሉ
ጥንታዊው መንደር ለጎብኚዎች ማራኪ መልከአ ምድርን የሚያጎናጽፍ ነው ተብሎለታል
በብዙ የየመን ከተሞች እና መንደሮች ውስጥ በአለት ላይ የተሰሩ ጥንታዊ ቤቶች መመልከት የተለመደ ነው፡፡
በተለይም ‘‘ሀይድ አል ጃዚል’’ ወይም ‘‘ታላቁ ተራራ’’ የሚል ትርጓሜ የተሰጠው፣በምስራቅ የመን ከሚገኙ ታላላቅ ሸለቆዎች አንዱ በሆነው፣ በዋዲ ዳዋን የሚገኘው ግዙፍ ድንጋያማ ተራራ በርካታ በዓለት ላይ የተሰሩ የጥንታዊ ቤቶች የሚታዩበት ስፍራ ነው፡፡
ሰነዶች እንደሚያስረዱት ከሆነ ጥንታውያን የመኖች ራሳቸውን ከጥቃት ለመሸሸግና ከተደጋጋሚ ወረራዎችን ለመከላከል በሚል መኖሪያ ቤታቸውን በገደል ቋጥኝ ላይ ይሰሩ ነበር፡፡
ሀይድ አል ጃዚል 500 አመታትን ያስቆጠረ ስፍራ እንደሆነም የታሪክ መዛግብት ያመለክታሉ፡፡
አስክሬን እየተሰረቀባት የተቸገረችው እንድሪያስ ገዳም
በእርሻ መሬቶች በተከበበና ከሸለቋማ ስፍራ 300 ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወደዚህ ቦታ ለመድረስ፤ በድንጋይ የተቀረፁ ደረጃዎች እንዲሁም አስር ሜትር የሚረዝም መንገድ፣ አስፈሪ ኩርባዎች እና ማማዎችን መውጣት ይጠይቃል፡፡
ከ 30 እስከ 40 ቤቶችን ያቀፈው ይህ መንደር፤ ለጎብኚዎች ማራኪ መልከዓ ምድርን የሚያጎናጽፍ፣ በውስጡ ቴምርን ጨምሮ የተለያዩ አትክልቶች እንዲሁም ሰብሎችን በያዙ እርሻዎች የተከበበ እንዲሁም በአቅራቢያውም ለመንደሩ ሰዎች ለመጠጥ ውሀ የሚውል ትንሽ ወንዝም ያለው ነው፡፡
የታሪክ እና የቅርስ ባለሙያ የሆኑት ዑመር ባግባር አል-አሙዲ ‘የሀይድ አል ጃዚል’’ ቤቶች የተገነቡት ከጭቃ እና ገለባ መሆናቸው ለአል ዐይን አል አክባር ተናግረዋል፡፡
ቤቶቹ ብዙ የእንጨት ንጣፎችን ያቀፉ እንደመሆናቸው በቀላሉ በመሬት መንቀጥቀጥ እና ለአየር ንብርት ለውጥ ተጋላጭ ሳይሆኑ ለዘመናት ሊዘልቁ ችለዋል ያሉት ባለሙያው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለውን የነዋሪዎቹን ፍልሰት ተከትሎ ፤ ቤቶቹ በእድሳት እጦት የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
‘‘አል-ጃዚል’’ የጎብኚዎች መዳረሻ እንዲሆን አስፈላጊ እድሳት ሊደረግለት ይገባልም ነው፤ የታሪክ እና የቅርስ ባለሙያው ዑመር ባግባር ያሉት፡፡