የየመን ጦር በሳዑዲ አረቢያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘውን ሀረዳህ ከተማ ከሀውሲ ለማውጣት መቃረቡን አስታውቋል
የየመን ጦር ስምንት የሃውሲ አማጽያን ድሮኖች ከጥቅም ውጪ ማድረጉን አስታወቀ።
አል ዐይን ኒውስ ከየመን ጦር ያነኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ጦሩ ድሮኖችን በትናትናው እለት በሃጃህ ግዛት በመብረር ላይ እያሉ ነው መትቶ የጣለው።
ዶሮኖቹ ተመትተው የወደቁት በምእራብ የመን በሚገኙ እና ከሃውሲ አማፅያን ነጻ በወጡ በሃጃህ ግዛት አካባቢዎች መሆኑንም ጦሩ ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ጦሩ በሃውሲ አማጽያን እጅ የምትገኘውን ሃራደህ ከተማ ነጻ ለማውጣት ዘመቻ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የየመን ጦር ሃጃህ ግዛትን ከአማጽያኑ ነጻ ለማውጣት የጀመረው ዘመቻ አራተኛ ቀኑን መያዙም የተነገረ ሲሆን፤ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ እንደሆነም ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅትም የየመን ጦር ሀረዳህ ከተማ ነጻ ለማውጣት በሶስት አቅጣጫዎች ማለተም በደቡብ፣ በምስራቅ እና በሰሜን በኩል ወደ ከተማዋ እየተቃረበ መሆኑንም ጦሩ በመግለጫውአ ስታውቋል።
አሁን እየተካሄደ ባለው ጦርነትን ከፍተኛ የሀውሲ አማጽያንን አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የብድኑ ታጣቂዎች መሞታቸውንም እንዲሁም በርካታ የጦር ተሸከርካሪዎችና መሳሪያዎች መውደማቸውንም በመግለጫው ተመላክቷል።
ሀረዳህ ከተማ በሳዑዲ ድንበር ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ የሀውሲ አማጽያን ሳዑዲን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትን የሚያጠቃዉ ከዚህ ከተማ በመነሳት ሳይሆን እንደላቀረ ይነገራል።
የሀውሲ አማጽያን ከሰሞኑ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ ላይ የድሮኖች እና በሚሳዔል በመታገስ ጥቃት መፈፀሙ ይታወሳል።