ብሪታንያ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ከስራ ውጪ ለሆኑ ሰዎች የክብደት መቀነሻ ክትባት ዘመቻ ጀመረች
ሀገሪቱ ለዚህ ዘመቻ 280 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት አዘጋጅቻለሁም ብላለች
ብሪታንያ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ምክንያት በዓመት 13 ቢሊዮን ዩሮ ታጣለች
ብሪታንያ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ከስራ ውጪ ለሆኑ ሰዎች የክብደት መቀነሻ ክትባት ዘመቻ ጀመረች፡፡
ከመጠን በላይ ውፍረት በዓለማችን ገዳይ ለሆኑ በሽታዎች ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን በተለይም ለስኳር፣ ልብ እና ለተለያዩ የካንሰር ህመሞች በመዳረግ ታወቃል፡፡
ብሪታንያ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት እየተጎዱ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ይህን ለመከላከል አዲስ ዘመቻ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡
ሀገሪቱ ከመጠን በላይ በሆነ ውፍረት ምክንያት ዜጎቿ ከስራ ውጪ በመሆናቸው ኢኮኖሚው እየተጎዳ ነው በሚል የውፍረት መቀነሻ ክትባት ዘመቻ መጀመሯን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ክትባቱን ለመስጠት 280 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት የተመደበ ሲሆን ከመጠን በላይ ውፍረት ምክንያት ከስራ የሆኑ ዜጎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ታስቧል፡፡
ክትባቱ ለሙከራ በማንችስተር ከተማ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደሚስፋፋ ተገልጿል፡፡
ብሪታንያ ከመጠን በላይ ውፍረት ምክንያት 13 ቢሊዮን ዩሮ እያጣች ነው የተባለ ሲሆን በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጠን በላይ ክብደት መከላከያ ክትባት እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡
ሙንጃሮ የተሰኘው የክብደት መቀነሻ መድሃኒት ከመጠን በላይ ውፍረትን ከመቀነሱ በላይ ለስኳር ህመምተኞችም ይሰጣል ተብሏል፡፡
የብሪታንያ ወንጀል ሚኒስትር ስለ ወንጀል መጨመር መግለጫ እየሰጡ እያለ የእጅ ቦርሳቸው ተሰረቀ
ከመጠን በላይ ውፍረት ሲጋራ ማጨስ ከሚያደርሰው ጉዳት በላይ በብሪታንያዊያን ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው የተባለ ሲሆን ከክትባቱ በኋላ ዜጎች ህመማቸውን ከማስታመም ወደ ስራ እንዲመለሱ በማድረግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚያነቃቃ ታምኖበታል፡፡
በብሪታንያው ሊሊ ኩባንያ የሚመረተው ሙንጃሮ የተሰኘው የክብደት መቀነሻ መድሃኒት በዓለም ላይ ካሉ ተመሳሳይ ምርቶች የተሻለ ውጤታማ ነው ተብሏል፡፡
ክትባቱ በብሪታንያዊያን ላይ በስፋት እየተሞከረ ሲሆን ውጤታማነቱ ከታየ በኋላ በቀጣይ ምርቱ ለዓለም ገበያ እንደሚቀርብም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡