ፖለቲካ
የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አስታወቁ
ዶ/ር ጌታቸው ከ3 ዓመታት በፊት በባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተርነት መሾማቸው ይታወሳል
ዋና ዳይሬክተሩ ምክንያታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ለመንግስት ማስገባታቸውን በተለይ ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ፡፡
በይፋ ኃላፊነታቸውን አለመልቀቃቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ጥያቄው በሂደት ላይ መሆኑን እና መንግስት ምላሽ ሲሰጥ በይፋ የሚለቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ምክንያታቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
ዶ/ር ጌታቸው ስልጣን ለቀዋል በሚል ከሰሞኑ ሲወራ ነበር፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር በመሆን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉት ዶ/ር ጌታቸው ከ3 ዓመታት በፊት 2011 ዓ/ም ወርሃ ሚያዚያ መባቻ ላይ ነበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተሾመው ባለስልጣኑን በዋና ዳይሬክተርነት መምራት የጀመሩት፡፡