“የአፍሪካን እና የህዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚባክን ነገር ሊኖር አይገባም”- የግብጽ ፕሬዝዳንት
መጪውን የፈረንጆች ዓመት (2022) ኮሚቴውን በሊቀመንበርነት ትመራለችም ተብሏል
ግብጽ ናይጄሪያን በመተካት የአፍሪካ የጸጥታ እና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመርጣለች
“የአፍሪካን እና የህዝቦቿን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚባክን ነገር ሊኖር አይገባም” ሲሉ የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ተናገሩ፡፡
ሲሲ ይህን የተናገሩት ትናንት እሁድ በካይሮ በተካሄደው 17ኛው የአፍሪካ የጸጥታ እና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ (CISSA) ጉባዔ ላይ በተላለፈ የቪደዮ ቅጂ መልዕክታቸው ነው፡፡
ለነባርና አዳዲስ የአፍሪካ የጸጥታና ደህንነት ችግሮች ምላሽ ለመስጠት መተባበር ያስፈልጋል ያሉት ሲሲ ሃገራቸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችል ደረጃ የኮሚቴውን አቅም ለማሳደግ ቃል ገብተዋል፡፡
በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ግብጻውያን ሊታገሱ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናገሩ
በተለይም ድንበር ዘለል በሆኑ የሽብር ተግባራት ላይ መተባበር እንደሚገባ ገልጸዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የኮሮና ወረርሽኝን ጭምሮ አህጉራዊ ስጋት ናቸው ስላሏቸው ስደት፣ ስራ አጥነት፣ የሳይበር እና ስለሌሎችም የተደራጁ ወንጀሎች አንስተዋል እንደ ጽህፈት ቤታቸው ገለጻ፡፡
ግብጽ የአፍሪካ የጸጥታ እና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆና ተመርጣለች፡፡ መጪውን የፈረንጆች ዓመትም (2022) ኮሚቴውን በሊቀመንበርነት ትመራለች፡፡ ኃላፊነቱንም ከናይጄሪያ ተረክባለች፡፡
በግብጽ ሲናይ በረሀ ጽንፈኞች አደረሱት በተባለ የሽበር ጥቃት 5 ወታደሮች ተገደሉ
በፈረንጆቹ 2004 በናይጄሪያ አቡጃ የተመሰረተው ኮሚቴው ለአፍሪካ ህብረት ግብዓት በሆኑ የጸጥታና ደህንነት ችግሮች ላይ ይሰራል፡፡ የህብረቱ አባል ሃገራት የደህንነት ተቋማትም አባላቱ ናቸው፡፡
የኮሚቴው ዋና ቢሮ አዲስ አበባ ነው የሚገኘው፡፡ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ 33ኛው የህብረቱ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባዔ ሲካሄድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡