የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሃገሪቱ ለ6 ወራት ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ማጽደቁን ተከትሎ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠይቋል።
ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይም በሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ እንዲነሳ መወሰኑን ኮሚሽኑ በበጎ እንደሚመለከተውም አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ሁኔታ ወቅት ከአዋጁ አተገባበር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ መንግስትን በድጋሚ ጠይቋል።
በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው የተለቀቁ ሰዎችም በእስር ስለመቆየታቸው ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ወደ ስራ መመለስ አለመቻልን ጨምሮ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ባደረገው ክትትል መገንዘቡንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
ሰዎች በእስር የቆዩበትን ጊዜ ማስረጃና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች የመስጠቱን ሂደት እንዲፋጠንና ሰዎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ እንዲችሉ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጊዜው ሳይደርስ ቀደም ብሎ እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ዛሬ ደግሞ ይህ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለት የሕዝብ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል።