በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታች በተመለከተ የሚመለከታቸው አካላትም ለኢሰመኮ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለባቸው- ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁን ተከትሎ መንግስት በቁጥጥር ስር ያደረጋቸው ሰዎች ሁኔታ እንደሚያሳስበው ገለጸ
ኢሰመኮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቆይታ፤ የሰብአዊ መብት ሁኔታችን እንደሚከታተልና የሚመለከታቸው ትብብር የማድረግ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡
“በአዲስ አበባ ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዎች ተይዘው እንደሚገኙ”ማረጋገጡን ኮመሽኑ አስታውቋል፡፡
በአዋጁ መንግስት የጠረጠረውን መያዝ ይችላል ያለው ኢሰመኮ “እስሩ ማንነትን/ብሔርን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል መከናወኑ” እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡
“ኢሰመኮ የሕግ አስከባሪ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና መመሪያዎቹን በሥራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያስፈጽሙ የሕጋዊነት፣ የጥብቅ አስፈላጊነትና ተመጣጣኝነት እንዲሁም ከመድልዎ ነፃ መሆን የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን” ማክበር አለበት ብሏል ኢሰመኮ፡፡
ኢሰመኮ የህግ አስከባሪ አካላት “በማንኛውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር፣ ተግባራቶቻቸውንም በከፍተኛ የሙያ ሥነምግባር በመመራት የማከናወን ኃላፊነት” እንዳለባቸውም አሳስቧል፡፡
በፌደራል ምንግስት የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፤ ኢትዮጵያን ለ27 አመታት ሲያስተዳድር የነበረውየገዥ ፓርቲ ግባሮች በመዋሃድ ብልጽግና ፓርቲን ሲመሰርቱ ህወሓት የውህደቱ አካል አልሆንም ብሎ በማፈንገጡ ነው።
ህወሓት የፌደራል መንግስቱ ህገወጥ ነው ያለውን ምርጫ ማካሄዱም የአልመግባባቱ ጡዘት ውጤት ነበር።
በሁለቱ አካላት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ወታራዊ ግጭት ያመራው፤ ጥቅምት 24፣2013 ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር፡፡
ክህደት ፈጽሟል ባለው ህወሓት ላይ “የህግ ማስከበር ዘመቻ” በማወጅ የትግራይ ዋና ከተማና ብዙ ቦታዎችን መያዝ የቻለው መንግስት ከ8 ወራት በኋላ ለትግራይ ህዝብ የጽሞና ግዜ ለመስጠት በማሰብ ከትግራይ ክልል ሰራዊቱን ማስወጣቱ ይታወሳል። በክልሉ በነበረው ጦርነት ወቅት ዜጎች መፈናቃላቸውንና መገደላቸውን ኢሰመኮና ሌሎች አለምአቀፍ ተቋማት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
መንግስት ጦሩን ከክልሉ ማስወጣቱን ተከትሎ፣ ሕወሓት ወደ አማራ አፋር ክልል በመግባት ጥቃት በመሰንዘር፤ ሰዎች እንዲገደሉና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉን መንግስት ገልጿል። አሁን ጦርነት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ህዝብ ለርሃብና ለሞት አደጋ የተዳረገ ሲሆን በ100ሺዎች የሚቆጠር ሰውም ጦርነቱን በመሸሽ እየተፈናቀሉ መሆናቸውን መንግስት እየገለጸ ይገኛሉ፡፡
መንግስት በኢትዮጵያ በሽብር የተፈረጀው ህወሓት ደቅኖታል ያለውን ሉአላዊነትን ችግር ውስጥ የሚያስገባ አደጋ ለመቀልበስ ባለፈው ሳምንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።