በወር 500 ሺህ የቺሊ ፔሶ ይከፈለው የነበረው ግለሰቡ በስህተት 165 ሚሊየን ፔሶ በላይ ተከፍሎታል
ቺሊዊው ግለሰብ በወር ይከፈለው የነበረ ደመወዙን በስህተት 286 እጥፍ እንደተከፈለው ከሰሞኑ ተሰምቷል።
ግለሰቡ ኮንሶርሲዮ ኢንዱስትሪያል ዲ አልሜንቶስ የሚባል ድርጅት ውስጥ ይሰራ ነበር ተብሏል።
ባሳለፍነው ወር ላይ 165 ሚሊየን 398 ሺህ 851 የቺሊ ፔሶ ወይም 180 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በስህተት እንደተከፈለው ተነግሯል።
ግለሰቡ የወር ደመወዙ 500 ሺህ የቺሊ ፔሶ ወይም 542 የአሜሪካ ዶላር እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፤ በስህተትም በአንድ ጊዜ የወር ደመወዙ 286 እጥፍ በባንክ ሂሳቡ ላይ እንደገባ ታውቋል።
ግሰለሰቡ ግዘቡን ለመመለስ ፍላጎት የለውም የተባለ ሲሆን፤ ለመስሪያ ቤቱ መልቀቂያ በማስገባት ደብዛውን ማጥፋቱ ም ተነግሯል።
አሁን ላይ የኩብናንው የህግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) ጉዳዩን በህግ መያዛቸውን እና የጠፋውን ሰራተኛ ዱካ ማፈላግ ላይ መሆናቸውን የቺሊው ዲያሪዮ ፊናንሴሮ ጋዜጣ አስነብቧል።