የመከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ስራ በዚህ ሳምንት ይከናወናል- አምባሳደር ሬድዋን
ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ክልል የተጀመረው አገልግሎት የማቅረብ ሥራ እንዲፋጠን መመሪያ ሰጥተዋል
ህወሓት የታጠቃቸውን ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ለመንግስት የማስረከብ ስራ እስከ ሀሙስ እንደሚፈፀም አስታውቀዋል
ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የማስረከብና መከላከያ በመቀሌ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ስራ በዚህ ሳምንት እንደሚከናወን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው የፌዴራል መንግሥት የልዑካን ቡድን በመቀሌ የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብራሪያ ማቅረቡን አስታውቀዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ በ2ኛው የናይሮቢ የሰላም ስምምነት መሠረት ህወሓት የታጠቃቸው ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ለመንግስት የማስረከብ ስራ እስከ ሀሙስ እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቀሌ መደበኛ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ
- በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
ማብራሪያውን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተጀመረው አገልግሎት የማቅረብ ሥራ እንዲፋጠን መመሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በመመሪያው መሠረትም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ በነገው ዕለት እንደሚጀምር እና ኢትዮ ቴሌኮምም በቅርቡ አገልግሎት የሚጀምርበትን ቀን ይፋ እንደሚያደርግም አማካሪው አስታውቀዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በትናትናው እለት በመቀሌ ቆይታ አድርጎ መመለሱ ይታወሳል።
በቆይታውም ከህወሓት አመራሮች እና ከመቀሌ ከተማ ከተውጣጡ የህብረሰተብ ክፍሎች ጋር በሰለ፤ም ስምምነቱ አተገባበር ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል።