በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና
የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ነው
ቡድኑ በቆይታው በሰላም በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ያደርጋል
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫ የተመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ ማቅናቱ ተሰማ።
የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ መሆኑንም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ መሆኑም ታውቋል።
አቶ ታገሰ ጫ የተመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ ማቅናቱ ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ እነሚታመን ማሳያ መሆኑንም መንግስት አስታውቋል።
ወደ መቀሌ ያመራው የፍደራል ምንግስት በልዑካን ቡድን ውስጥ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም መካተታቸወን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
- የፌደራል መንግስትና የህወሓት አመራሮች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቀሌ ላይ ተገናኝተው ይመክራሉ ተባለ
- የፌደራል መንግስት እና ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ማስፈጸሚያ እቅድ ተፈራረሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትናትናው እለት የናይሮቢ ሁለተኛውን ውይይት ተከትሎ የሰላም ሂደቱን መገምገማቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።
በግገማውም የሰላም ስምምነቱ የትግበራ ሂደት ተስፋ ሰጪ መሆኑን መለየታውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አሁንም ለሰላም ባለን ቁርጠኝነት ጸንተናል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ሃይሎች የጦር አዛዦች በኬንያ ናይሮቢ በድጋሚ ለሁለት ቀናት ያደረጉት ምክክር መጠናቀቁን ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ ተሰጥቷል።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታም በመግለጫው ላይ የአፍሪካ ህብረት የታዛቢ ቡድን በሰላም ስምምነቱ የተጠቀሱ ነጥቦች ተፈጻሚነታቸውን ለማረጋገጥ በጥቂት ቀናት ውስጥ መቀሌ ይገባል ማለታቸውም ይታወሳል።
የፌደራል መንግስትና የህወሓት አመራሮች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቀሌ ላይ ተገናኝተው በቀሪ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም በናይሮቢው መግለጫ ላይ መነሳቱ ይታወሳል።