ፑቲን ስለሩሲያ እና ምዕራባዊያን ንግግር ጉዳይ ለመወያየት ኤርዶጋንን ሊያገኙ ይችላሉ ተባለ
ፑቲን እና ኤርዶጋን በዚህ ሳምንት ካዛኪስታንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል
ፑቲን እና ኤርዶጋን በዚህ ሳምንት ካዛኪስታንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል
ፕሬዝዳንት ፑቲን የቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋንን በዚህ ሳምንት ሊያነጋግሩ እንደሚችሉ ሮይተርስ ዘግቧል።
ቱርክ በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል በዩክሬን ጉዳይ የሚደረጉ ውይይቶችን ለማስተናገድ ባቀረበችው ሀሳብ ላይ ፑቲን እና ኤርዶጋን ሊወያዩ ይችላሉ ሲል ክሬምሊን አስታውቋል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሩሲያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር በቱርክ ልታደርገው ስላለው ድርድር ምንም አይነት ምልክት እንዳልደረሳት ገልፀው ነገር ግን ፑቲን ከኤርዶጋን ጋር ሊወያዩ እንደሚችሉ አልገለጹም።
ፑቲን እና ኤርዶጋን በዚህ ሳምንት ካዛኪስታንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለሰባት ወራት የዘለቀው የዩክሬን ጦርነት በምዕራቡ ዓለም እና ሩሲያ መካከል ያለው ውጥረት አሁንም እየጨመረ ነው።
ሩሲያ በሰራችው እና ወደ ክራይሚያ የሚወስደውን ድልድይ ክፉኛ ከተጎዳ በኋላ ሞስኮ ሰኞ እለት በመላው ዩክሬን የሚሳኤል ጥቃት አድርጋለች።
ከሞስኮ እና ከኪየቭ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላት ቱርክ በግጭቱ ውስጥ አስታራቂ ሆና ታይታለች።
ቱርክ በሐምሌ ወር በጥቁር ባህር ወደቦች የታገደውን የዩክሬን እህል ወደ ውጭ ለመላክ እንዲቻል አድርጋለች።
ኤርዶጋን ፑቲን ውጥረቱን እንዲቀንስ አሳስበዋል፤ በመስከሰም ላይ ሞስኮ ለሰላም ድርድር ሌላ ዕድል እንድትሰጥ ጠይቋል።
ኋይት ሀውስ እሁድ እለት እንዳስታወቀው ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን የሚያቆሙበትን መንገድ መፈለግ አለባቸው ብሏል።