ኤርትራና ግብጽ በኢትዮጵያ ግድብና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያዩ- የማነ ገ/መስቀል
ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 76 ወታደራዊ አመራሮች የእስር ማዘዣ ወጣባቸው
መንግስት በህወሓት ሃይሎች ላይ በምስራቅና በምእራብ ድል ማድረጉን እያሳወቀ ባለበት ወቅት ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከግብጽ ጋር መምከሯን ገለጸች
መንግስት በህወሓት ሃይሎች ላይ በምስራቅና በምእራብ ድል ማድረጉን እያሳወቀ ባለበት ወቅት ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከግብጽ ጋር መምከሯን ገለጸች
የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው በህዳሴው ግድብ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ውይይትና በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኤርትራ ሉኡኳን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህና የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አማካሪ በሆኑት የማነ ገብረአብ የተመራ ሲሆን በግብጽ ካይሮ ሲደርሱ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሾከሪ አቀባበል እንደተደረገላቸው ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገልጸዋል፡፡
ስብሰባው ሁለቱ ሀገራት የሚያካሄዱት መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ አካል እንደሆነና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ሚኒስትሩ ጽፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ሃይሎች ላይ በምስራቅና በምእራብ ግንባር በርካታ ቦታዎች መቆጣጠሩን እያሳወቀ ባለበት ወቅት ጎረቤት ሀገር ኤርትራ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከሯን አስታውቃለች፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥቅምት 24 ህወሓት በትግራይ ክልል ባለው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፈጸመው ጥቃት ላይ እርምዳ እንደሚወስዱም አስታውቀው ነበር፡፡
በዛሬ እለት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀገር ክደዋል የተባሉ 76 ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች የመያዣ ትእዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል
ኮሚሽኑ ከሕወሓት “የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እጃቸውን ባስገቡና በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራው” ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ሲያካሄዱት የነበረውን ድርድር ኢትዮጵያ ባለመስማማቷ ምክንያት ካተቋረጡ በኋላ ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት ማእቀፍ እየተደራደሩ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው ክረምት ወቅት 4.9 ሚሊዮን ኪቡክ ሜትር ውሃ ግድቡ መጀመሪያ ምእራፍ እንዲይዝ አድርጋለች፡፡