“አሜሪካን መሰል ሃገራት የህወሓትን ወንጀሎች በመሸፈን እንዲያንሰራራ ለማድረግ የያዙት አቋም ይቅር የማይባል ነው”- ኤርትራ
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ76ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው
ኡስማን ሳሌህ ህወሓት የፈጸማቸው “አረመኔያዊ እና ህገወጥ ድርጊቶች”ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ጭምር እጅግ አሳሳቢ ለመሆኑ ማሳያ ናቸው ብለዋል
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 76ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በቪዲዮ ቀድሞ በተቀረፀ መልዕክት ንግግር አድርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ በሐምሌ ወር 2018 የፈረሙት የሰላም እና የወዳጅነት ስምምነት “በሀገራቱ መካከል አዲስ የተስፋ ዘመንን አስገኝቷል፤ በህዝቦች መካከል የፈጠረው ደስታም የታሪካዊ ስምምነቱን ትርጉም እና ስኬት በግልጽ ያሳየ ነው” ብለዋል።
ሆኖም ግን ህወሓት ይህን ነባራዊ ሁኔታ “መቀበል ተስኖታል”፡፡ የሰላም ሂደቱን ለማኮላሸት እና በኢትዮጵያ ያጣውን ስልጣን በሀይል መልሶ ለመያዝ በርካታ አፍራሽ ድርጊቶችን ማካሄድ ጀምሯል እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ።
ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ንግግራቸው ምን አሉ?
ህወሓት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ ለሁለት አስርት ዓመታት ገደማ ሉዓላዊ የኤርትራ ግዛቶችን ይዞ መቆየቱንም ያስታወሱት ሳሌህ በዚህ ጊዜ ሁሉ ጦርነት ለመቀስቀስ በኤርትራ ላይ የማያቋርጡ ትንኮሳዎችን ያደርግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ስምምነት እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ፍላጎት እየተካሄደ ያለውን አዎንታዊ የለውጥ ሂደት ወደ ኋላ ለመመለስ የተለያዩ ህገወጥ የጥፋት ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነም ገልፀዋል።
በዚህም የህወሓት ቡድን የጦር መሳሪያን በመዝረፍ ስልጣንን በሀይል መልሶ ለመያዝ በማሰብ የሰሜን እዝን ማጥቃቱን ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ አላማው በኤርትራ ላይ ቀጣይ ወታደራዊ ጥቃቶችን መሰንዘርን ጭምር ያካተተ እንደነበርም ተናግረዋል።
“ተንኮለኛ” ያሉት ቡድኑ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የፈጸማቸው “አረመኔያዊ እና ህገወጥ ድርጊቶች”ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ጭምር እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ለማሳየት ተጨማሪ ማስረጃ እንደማይፈልጉም ሳሌህ በንግግራቸው አስቀምጠዋል፡፡
ሆኖም ግን አሜሪካ እና አውሮፓን ጨምሮ የተወሰኑ ሀገራት የቡድኑን “አደገኛ እና ህገ ወጥ ድርጊቶች በመሸፈን” ቡድኑን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያደርጉት ጥረት “ይቅር ሊባል የማይችል ነው” ብለዋል።
አሜሪካ ህወሓት ሕፃናትን ለወታደርነት “እየመለመለ ነው”መባሉ እንዳሳሰባት ገለጸች
በዚህ “ዋና ወንጀለኛ ቡድን” እና በራሳቸውና በዓለም አቀፍ ህግጋት መሰረት የአጸፋ እርምጃዎችን ለመውሰድ በተገደዱት መካከል “የሞራል እኩሌታ”ን ለመፍጠር የሚነዟቸውን የሃሰት ትርክቶች በመዘርዘር ጊዜያችሁን አላባክንምም ነው ሳሌህ በንግግራቸው ያሉት፡፡
የህወሓት አጋር የሆኑ ሀገራት እና ተቋማት አሁን እየፈፀሙት ያለው ድርጊት በአለም አቀፉ የአስተዳደር ስርዓት ያለውን ከፍተት ያሳያል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ባሉት ተመሳሳይ ድርጊቶች ኤርትራ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባታል፤ ይህ እንደገና መደገም የለበትም ብለዋል።