ኢኮኖሚ
እስያ የታዳሽ ኃይል እርምጃን በመምራት ቀዳሚ ናት
በእስያ መንግስታትና የኢንዱስትሪ መሪዎች መሬት የረገጡ የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንቶች እየተደረጉ ነው
ጃፓን ወደ ታዳሽና ንጹህ ኃይል የሚደረገውን ሽግግር ለመደገፍ 10 ቢሊዮን ዶላር መድባለች
መንግስታት የኃይል አማራጮችን እንዲያማትሩ የገንዘብ አቅርቦት ላይ ጫና እየደረሰባቸው ነው።
በእስያ መንግስታትና የኢንዱስትሪ መሪዎች መሬት የረገጡ የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንቶች እየተደረጉ ናቸው።
ይህም ኪሳራ እንደደረሰባት ዩናይትድ ኪንግደም ካሉ ሀገራት ተመሳሳይ እጣ እንዳይደርስባቸው አድርጓል።
የግሪን ኃይድሮጅን የኃይል አማራጭ አይን የተጣለበት ሲሆን፤ ሀገራት አቅማቸውን ለማጠናከር በፍጥነት ለማልማት ገንዘብ እየመደቡ ነው።
የኃይል አማራጭን ማሳደግና ታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂን ማሳደግ ላይ ትኩረት ቢጣልም፤ ለእስያ ሀገራት የግሪን ኃይድሮጅን እመርታ ቅድሚያ እያገኘ ነው።
የኃይድሮጅን ምክር ቤት የግመታ ሪፖርት እንደሚያስቀምጠው በእስያ አህጉረ በ2030 የ90 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል።
የአህጉሪቱን የኃይል አሰላለፍ እየመራች ያለችው ጃፓን፤ ወደ ታዳሽና ንጹህ ኃይል የሚደረገውን ሽግግር ለመደገፍ 10 ቢሊዮን ዶላር መድባለች።
ሀገሪቱ ኃይድሮጅንን ኢኮኖሚዋን ከካርቦን ልቀት ለማላቀቅና እንደ ቁልፍ የኃይል አማራጭ አድርጋ ትመለከታለች።
ህንድ ደግሞ በእስያ የኃይል ገበያ ብቅ ያለች አዲሷ ሀገር ሆናለች።