በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር የነበረው ግጭት ተፈትቷል፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የሚኖሩ ህዝቦች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል ተባለ
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የነበረው ግጭት በመፈታቱ በድንበር አካባቢ ያሉት ህዝቦች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል ተባለ
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር የነበረው ግጭት በመፈታቱ በድንበር አካባቢ ያሉት ህዝቦች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል ተባለ
ከሰሞኑ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ ላይ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መቆሙን እና በድንበር የሚኖሩ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችም ወደ ተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ ተጠባባቂ ቃል አቀባይ አምሳሉ ትዕዛዙ የአካባቢዎቹ የሥራ ሃላፊዎች ግጭት ተከስቶባቸው የነበሩ ቦታዎችን መጎብኘታቸውንና ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው ችግር መቀረፉን ለአል ዐይን ገልጸዋል፡፡
አቶ አምሳሉ “የተፈጠረው ችግር አሳዛኝ እና መሆን ያልነበረበት” መሆኑን ገልጸው አሁን ግን ችግሩ መቀረፉን ገልጸዋል፡፡ ሁለቱም ሀገራት የድንበር ላይ ነዋሪዎች የተለመደ ማህበራዊ ኑሯቸውን በትብብር እየመሩ መሆኑንም አቶ አምሳሉ ተናግረዋል ። አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ወደ ተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውንም አቶ አምሳሉ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ሱዳን “የኢትዮጵያ ታጣቂዎች” በመከላከያ በመታገዝ ድንበር ጥሰው ጥቃት አድርሰዋል በማለት በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተወካይን ጠርታ እስከማነጋገር ደርሳ ነበር፡፡ ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ወደ ግጭት የሚያደርስ ነገር እንደሌለና ችግሩ በዲፖሎማሲያዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ገልጻ ነበር፡፡
በሱዳን በኩል አሁን ያለውን ሁኔታ የሚመለከት መግለጫ አልወጣም፡፡