በዩኤኢ ለኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያን የሚሰሩበት ቦታ ተሰጣቸው
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን አስመልክቶ በዩኤኢ ዝግጅት ሊደረግ ነው
በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች (ዩኤኢ) የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ተከትሎ ዝግጅት ሊደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና የዩኤኢ ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴዔታ ሪም አልሃሽሜ ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
የዩኤኢ ባለሃብቶች በግብርና መስክ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው እና ኢትዮጵያ በዱባይ በሚካሄደው ኤክስፖ2020 ልዩ ቦታ እንደተሰጣት በውይይቱ ተነስቷል።
በተጨማሪም በዩኤኢ የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ቤተ ክርስቲያን የሚሰሩበት ቦታ እንደተሰጣቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ አንስተዋል።
የኢትዮጵያና ዩኤኢ ግንኙነት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከፍ ብሏል፤ ዩኤኢ በአዲስ አባበ ለኢንቨስትመንት ቦታ ስታገኝ ኢትዮጵያ ደግሞ ከዩኤኢ ብድር ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡