ኢትዮጵያ የተመድ የጸጥታው ም/ቤት የግድቡን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመልሰው ጠየቀች
“እኛ እየገነባን ያለነው የኃይል ማመንጫ ግድብ ነው፤ ይህ ደግሞ በአፍሪካም ሆነ በአለም በአይነቱ የተለየ አይደለም፡”
ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ “ከመካከለኛው ምስራቅ በባዶ እግራቸው ሲመለሱ ያያችኋቸው ስደተኞች ክብር ያለው ህይወት ይገባቸዋል” ብለዋል
የኢትዮጵያ ውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የጸጥታው ም/ቤት የግድቡን ጉዳይ አግባብነት ላለው የአፍሪካ ህብረት አመራር እንዲመልሰውና ግብጽና ሱዳንም በግድቡ ሙሌትና አስተዳደር ላይ በቅን ልብ ከስምምነት እንዲስማሙ እንዲያበረታታ ጠይቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የተመድ የጽጥታው ምክርቤት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባቸው ባለችው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲካድ ብትፈልግም ግብጽና ሱዳን የግድቡ ጉዳይ የደህንነት ስጋት ነው በሚል ወደ ተመድ የጸጥታው ም/ቤት እንዲደርስ አድርገውታል፡፡
የኢትዮጵያ 2/3 የሚሆኑው የውሃ ሃብት በአባይ ተፋሰስ ውስጥ እንደሚገኝ ለም/ቤቱ ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያውን፣ ኢትዮጵያ ከአባይ ውሃ መጠቀም አለመቻላቸው እንደሚያስቆጫቸው አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትር ስለሺ ኢትዮጵያውያን ወንዝ እያለ መጠቀም አለመቻላቸውን “‘የአባይን ልጅ ወሃ ጠማው’” በሚል አባባል በቁጭት እንደሚገልጹትም ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ይህን የቆየ ቁጭት እውን ለማድረግ ወደ አባይ ወንዝ እንድንመለስ ተገደናል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ “የሃይል ማመንጫ ግድብ ከተጠበቀው በላይ ምርመራ በሚገኝበት በዚህ ስብባብ ይህን ምክርቤት በዚህ ጉዳይ ሳስረዳ ብቸኛ የውሃ ሚኒስቴር አለመሆኔን እግጠኛ አይደለሁም፡፡ ኢትዮጵያ የተመድ የጥታው ምክርቤት በኢትጵያ ግድብ ጉዳይ ጊዜና ገንዘብ መድቦ መሰብሰቡ አግባባይ አይደለም ብላ ታምናለች”
ከአንድ አመት በፊት የተመድ የጸጥታው ም/ቤቱ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መስማማት ያልቻሉባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ሆነው በሚያካሂዱት ውይይት እንዲፈቱና ውይይቱን እንዲቀጥሉ አበረታቶም እንደነበር ሚኒስትሩ በስብባው አስታውሰዋል፡፡
ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ኢትዮጵያ በበጎ መልኩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚካሄደውን ድረድር በቁርጠኝነት ትሳተፋለች፤የደቡብ አፍሪካንና የኮንጎን ፕሬዘዳንቶች በድርድሩ ያደረጉት ተግባር የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡
“እኛ እየገነባን ያለነው የኃይል ማመንጫ ግድብ ነው፤ ይህ ደግሞ በአፍሪካም ሆነ በአለም በአይነቱ የተለየ አይደለም፡፡ ውሃ የሚይይዝ ማጠራቀሚያ ነው እየገነባን ያለው፣ ተርባይን በመምታት ኤሌክትሪክ የሚያመነጭ ነው፤ የግድቡ ሪዘርቪየርም ከአስዋን ግድብ ከሁለት እጥፍ በላይ የሚያንስ ነው፤ግድቡ ምናልባት ከሌሎች ፕሮጀክቶች የሚለየው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለሌላቸው 65 ሚሊዮን ኢትጵያውያን የሚያመነጨው ተስፋና ጉጉት ነው፡፡”
70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ከ30 አመት በታች መሆኑን የተናሩት ሚኒስትሩ የዚህን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት የግድብ ልማት አስፈላጊና የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሲ በችግር ምክንያት ኢትጵያውያን ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሲሞክሩ ሰሃራ በረሃ እየቀሩ ነው፤ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ስደተኞች በእስርቤቶች እየማቀቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
“ከመካከለኛው ምስራቅ በባዶ እግራቸው ሲመለሱ ያያችኋቸው [ኢትዮጵያውያን] ስደተኞች ክብር ያለው ህይወት ይገባቸዋል” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ሚኒስትሩ ግድቡ የህዝብ ፕሮጀክት ስለሆነ ብዙ ችግሮች ሊጋጥሙ ቢችሉም እውን እናደርገዋለን በማት ለም/ቤቱ ተናግረዋል፡፡ግብጽና ሰዱን በቅርቡ ግድቡን በጽኑ እየተቃውሙ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ እየተቃወሙ ያሉት ግድቡን ሳይሆን የኢትዮጵያን የውሃ ተጠቃሚነት ነው ብሎ ለመደምደም እንገደዳለን ብለዋል፡፡
ነገርግን ኢትዮጵያ እንደ ሱዳንና ግብጽ የሚጣራና ይህ ነው የሚባል የከርሰምድር ውሃ ስለሌላት የአባይን ውሃ መጠቀሟ የግድ እንደሚሆንባት ለም/ቤቱ አስረድታለች፡፡ ግብጹና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ወደሚከታተለው የተመድ የጸጥታው ም/ቤት ማምጣታቸው የሚያጸጸት እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ መሰረታዊ ችግሩ ሁለቱ ሀገራት የሚያራምዱት የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው ድርድር ቁርጠኛ መሆኗንና ግብጻውያንና ሱዳናውያንም መፍትሄው የሚገኘው ከጸጥታው ም/ቤት ሳይሆን በቅን ልበ ከሚደረግ ድርድር ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ከግድቡ መጀመር አንስቶ ውዝግብ ላይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ ከድህነት መውጫ የሚሆን የሃይል ማመንጫ መሆኑንና በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ ግብጽና ሱዳን በአንጻሩ በግድቡ ላይ የተለያየ ስጋት አላቸው፤በተለይ ግብጽ ታሪካዊ የውሃ ድርሻየ ይቀንሳል የሚል ስጋት ማንሳቷን እስካሁን ቀጥላበታለች፡፡