ፖለቲካ
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል ያለቻቸውን 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች
የዩኤን ኦቻ የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ሜሪ ቪጎዳም በአስቸኳይ ውጡ ከተባሉት መካከል ናቸው
በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ከታዘዙት መካከል የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ይገኙበታል
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል ያለቻቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰባት ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች፡፡
በሶስት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ የማሳሰቢያ ደብዳቤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከወጣባቸው የድርጅቱ ሰራተኞች መካከል የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር ይገኙበታል፡፡
የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ዩኤን ኦቻ) የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ ሜሪ ቪጎዳ በአስቸኳይ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ከተሰጣቸው ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል፡፡
ከእነዚህ በተጨማሪ
ሶኒ ኦንዬግቡላ የዩኤን ኦቻ የሞኒተሪንግ፣ ሪፖርቲንግ እና አድቮኬሲ ቡድን መሪ፣
ክዌሲ ሳንስኩሎቴ የሰላም እና ልማት አመካሪ፣
ሰዒድ መሃመድ ሂርሲ የዩኤን ኦቻ የኢትዮጵያ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣
ግራንት ሊዐይቲ የቢሮው ምክትል ሰብዓዊ አስተባባሪ እና
ጋዳ ኤልጣሂር ሙዳዊ የቢሮው ተጠባባቂ ሰብዓዊ አስተባባሪ ኢትዮጵያን በ72 ሰዓታት ውስ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጻፍኩ ያለው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡