በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ- መንግስት
መንግስት “የመሥዋዕትነት ሰልፍ አዘጋጅ ” በሚል ከባለ ሀብቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከወጣትቶ” የተውጣጣ ቡድን መዋቀሩን ደርሼበታለሁ ብሏል
“የመሥዋዕትነት ሰልፍ አዘጋጅ ” በሚል ከባለ ሀብቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከ”መንፈሳውያን የወጣት አደረጃጀቶች” የተውጣጣ ቡድን መዋቀሩን ደርሼበታለሁ ብሏል
“የመሥዋዕትነት ሰልፍ” ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ የሌለ በመሆኑ ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ ውስጥ የሚገባ መሆኑን መንግስት አሳስቧል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በውስጥ አሠራር እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙ አስታውሶ፤ ለዚህምም የሀገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸዉ ሁሉ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
- መንግስት ስለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ሰልፍ እንዳይደረግ ከለከለ
- ቤተክርስቲያኗ የጠራችው ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይ ይካሄዳል - ቅዱስ ሲኖዶስ
“በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው ልዩነትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዉስጣዊ አሠራርና ከዚያም ካለፈ በፍትሐ ብሔር ዳኝነት የሚታይ ነው” ያለው መግለጫው፤ “አስፈጻሚው አካልም በፍርድ ቤት ሲወሰን ብቻ የማስፈጸም ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ይታወቃል” ብሏል።
“ሆኖም ግን አጋጣሚዉን ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላት እየተገለጡ መሆኑን በልዩ ልዩ መንገዶች አረጋግጫለሁ ብሏል መንግስት በመግለጫው።
“የመሥዋዕትነት ሰልፍ አዘጋጅ ” በሚል ከባለ ሀብቶች፣ ከፖለቲከኞች እና ከ”መንፈሳውያን የወጣት አደረጃጀቶች” የተውጣጣ ቡድን ከማዕከል እስከ ታች መዋቀሩን መንግሥት እንደደረሰበትም አስታውቋል።
“የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም የሚሞክሩ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል” ያለው የመንግስት መግለጫ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመጠቀም የሰዎችንና የእምነት ተቋማትን መብቶች በመጣስ የመንግሥትን መልካም ስም ለማጥፋት የሚፈልጉ ሥውር እጆች እንዳሉም ማሰቁንም ጠቅሷል።
“ጉዳዩ ቀይ መሥመር ያለፈ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ የመሥዋዕትነት ሰልፍ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ የለም” ያለው መንግስት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ ዉስጥ የሚገባ መሆኑንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጠራችው ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ስልፍ “ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ” እንደሚካሄድ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።
በዚህም ለፊታችን የካቲት 5 2015 የተጠራው ሰልፍ በቤተክርስቲያኗ አደባባዮች ያለማንም ጫና እንደሚካሄዱ በቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ተጠቅሷል።
የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ትናንት ባወጣው መግለጫ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ሆነች “ህገወጥ ብላ የፈረጀችው ቡድን” የጠሩት ሰልፍ እንዳይካሄዱ መከልከሉ ይታወሳል።
ግብርሃይሉ ባወጣው መግለጫ "ህገወጥ የሰልፍ ጥሪዎች" ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ያለ ሲሆን፥ "በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ" የሰልፍ ጥሪ በማድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱ ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን ገልጿል።