ኢትዮጵያ በፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሴቶች ቁጥር ካላቸው የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ ነች- ተመድ
ሩዋንዳ በፓራላመዋ 61.3 በመቶ ሴት የፓርላማ አባላት ያላት በዓለም ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗ ይታወቃል
ኢትዮጵያውያን ሴቶች በፖለቲካው መስክ ያላቸውን ውክልና 42.5 በመቶ መድረሱን ተመድ አስታወቀ
ኢትዮጵያ በፓርላማ ከፍተኛ የሴቶች ቁጥር ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት ተርታ እንደምትሰለፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሴቶች ቁጥር ካላቸው (ማለትም ከ 40 በመቶ በላይ የሴቶች ውክልና) ካስመዘገቡት 25 ሀገራት መካከል አምስት የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ያለው ተመድ፤ ከእነዚህም ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗ በሪፖርቱ አመላክቷል።
ኢትዮጵያውያን ሴቶች በፖለቲካው መስክ ያላቸው ውክልና 42.5 በመቶ ደርሷልም ብሏል።
እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ሩዋንዳ (በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የ61.3 በመቶ የሴቶች ተሳትፎ)፣ ደቡብ አፍሪካ (46.3 በመቶ)፣ ናሚቢያ (46.3 በመቶ) እንዲሁም ሞዛምቢክ (44.2 በመቶ) የተሻለ የሴቶች የፖለቲካ ውክልና ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጭምር አስታውቋል።
በተለይም የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ሴቶች በፖለቲካ ተቋማት ላይ ያላቸውን ውክልና በማሳደግ ረገድ እድገት እያሳየ ያለ አከባቢ መሆኑን ተመድ በፖርቱ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ኡጋንዳ ሴቶች ሴቶች በፕሬዝዳንትነት እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት የኃላፊነት ቦታ የሚያገለግሉባቸው ሀገራት መሆናቸውንም እንደ አብነት አንስቷል።
ተመድ በቀጠናውም ሆነ በአፍሪካ የሴቶችን የፖለቲካ ውክልናን በማሳደረግ ረገድ ለውጦች ቢኖሩም፤ በውሳኔ ሰጪ ተቋማት ላይ ያለው ውክልና አሁንም ድረስ ክፈተቶች እንደሚስተዋልበት አስታውቋል።
ለዚህም በምርጫ ጽ/ቤት ውስጥ ጨምሮ በውሳኔ ሰጭ የስራ መደቦች ውስጥ ለጾታ እኩልነት የተሰጠው ትኩረት፣ የተዛቡ አመለካከቶች፣ አድሎአዊ ህጎች እና ፖሊሲዎች ሴቶች በፓለቲካው መስክ ተገቢውን ሚና እንዳይጫወቱ ከሚያደረጉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች ናቸው።