ኢትዮጵያ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው ቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት ውድድር ሆኖ አልፏል
ኢትዮጵያ እና ያለፉት አምስት የኦሎምፒክ ውድድሮች
የኦሎምፒክ ውድድር በየ አራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮውን የፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ባሳለፍነው ሳምንት ማዘጋጀቷ አይዘነጋም፡፡
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ በተለይም በሩጫ ዘርፍ ስኬታማ ሀገር ስትሆን በሁሉም ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 24 ወርቅ 15 ብር እና 23 ነሀስ በድምሩ 62 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡
ያለፉ አምስት የኦሎምፒክ ውድድሮችን ስንመለከት 10 ወርቅ፣ 10 ብር እንዲሁም 11 ነሀስ በድምሩ ኢትዮጵያ 32 ሜዳሊያዎችን ማፈግኘት ችላለች፡፡
ከ16 ዓመት በፊት የተካሄደው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በታሪኳ ከሲዲኒ ኦሎምፒክ በመቀጠል አራት ወርቅ በማግኘት ስኬታማ የሆነችበት ውድድር ነበር፡፡
እንዲሁም ከአራት ዓመት በፊት የተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ደግሞ አንድ ወርቅ አንድ ብር እና አንድ ነሀስ ዝቅተኛ ሜዳሊያ በማግኘት ዝቅተኛ ደረጃ ያገኘችበት የኦሎምፒክ ውድድር ተብሏል፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የፓሪስ ኦሎምፒክ አንድ ወርቅ እና ሶስት ብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 47 ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡