ፖለቲካ
“ ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ አንፈልግም” አምባሳደር ዲና
ሱዳን ወደነበረችበት በተመለሰች በደቂቃዎች ውስጥ ድርድር መጀመር እንደሚቻል ኢትዮጵያ ገልጻለች
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ “ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ አንፈልግም” ብለዋል፡፡ ከድንበር ውዝግቡም ጋር በተያያዘ ሱዳን እንደ አውሮፓውያኑ ከህዳር 6 ጀምሮ ከያዘችው መሬት ለቃ ሳትወጣ ኢትዮጵያ ለድርድር እንደማትቀመጥ አምባሳደር ዲና በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ ”የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ መተናኮል ለሱዳን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንባታል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡