አምባሳደሮችን ወደ ሀገርቤት መጥራት ከግድቡ ጋር የተያያዘ አይደለም-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አምባሳደሮችን ወደ ሀገርቤት መጥራት ከግድቡ ጋር የተያያዘ አይደለም-ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
መንግስት ኢትዮጵያን በውጭ ሀገራት የሚወክሉ 8 አምሳደሮችን ወደ ሀገርቤት እንዲመለሱ ጠርቷል፡፡
በሱዳንና በግብፅ ኢትዮጵያን የወከሉ አምባሳደሮች ከተጠሩት መካከል ይገኙበታል፡፡
ጥሪው ኢትዮጵያ በአሜሪካ በተካሄደውና የመጨረሻ በተባለው የፊርማ ስምምነት ላይ እንደማትገኝ ከገለጸች በኋላና አሜሪካ “ስምምነት ላይ ሳይደረስ የግድቡ የውሃ ሙሌት መጀመር የለበትም” ማለቷን ተከትሎ የመጣ በመሆኑ አንዳንዶች ከሰሞነኛው የህዳሴ ግድብ ድርድር አለመግባባት ጋር ሲያይዙት ይስተዋላል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው፣ አል ዐይን ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ግን ጥሪው መደበኛ እንጅ ከግድቡ ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል።
ከተጠሩት አምባሳደሮች መካከል ኢትዮጵያን በቤልጀም፣በግብጽ፣በሱዳን፣በእንግሊዝ የሚወክሉ ይገኙበታል።
በቤልጀም የኢትዮጵያ አምባሳደር ግሩም አባይ፣ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ፤ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍሰሀ ሻውል ናቸው፡፡
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ወደ ቀድሞ ቦታቸው በመመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ይመደባሉ የሚሉ ግምቶች አሉ።