ሀገሪቱ በቀጣዩ ዓመት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ማቀዷን አስታውቃለች
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሀና አርዓያ ስላሴ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሀገሪቱ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ውስጥ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር መሳቧን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ 329 የኢንቨስትመንቶች ፕሮጀክቶች ውስጥ 227ቱ የውጭ ባለሀብቶች ሲሆኑ ቀሪው ደግሞ በሽርክና እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ናቸው ተብሏል፡፡
ዘንድሮ የተገኘው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ11 በመቶ ብልጫ ሲኖረው በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ 4 ነትብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሳብ እንደታቀደ ኮሚሽነሯ ገልጸዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ከውጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች የተባለ ሲሆን ገቢው ከእቅዱ አንጻር የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት ማሳየቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒቴር አስታውቋል፡፡