በስኬቶቹ ተደስቻለሁ ያሉት ኢንጂነር ታከለ “በፍጹም ቅንነት ላጎደልናቸው ነገሮችም ይቅርታ እጠይቃለሁ!” ብለዋል
በስኬቶቹ ተደስቻለሁ ያሉት ኢንጂነር ታከለ “በፍጹም ቅንነት ላጎደልናቸው ነገሮችም ይቅርታ እጠይቃለሁ!” ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩትን ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከነበሩነት የስራ ኃላፊነት በማንሳት የማእድንና ኢነርጂ ሚኒሰትር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡
ኢንጂነር ታከላ “አዲስ አበባን መመራት ትልቅ እድል” እንደነበርና በኃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት አዲስ አበባን አንደ ስሟ አዲስ ለማድረግ መስራታቸውን ተናግረዋል፤ በሂደቱ ለረዷቸው አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢንጂነሩ በኃላፊነት ላይ ሳሉ በቅንነት ላጎደሏቸው ነገሮች ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
“አዲስ አበባን መምራት ትልቅ ዕድል ነው። ደጋግመን እንደምንለው፤ “በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን እድል” ላለማባከን ጥረናል። በሁሉም ውስጥ የነዋሪዎቻችን ብርቱ ድጋፍ አብሮን ነበር። አዲስ አበባን እንደስሟ ለማድረግ በደስታ፤ በፍላጎትና በፍቅር ስንተጋ ምርኩዝ ለሆናችሁን ሁሉ፤ ከልቤ አመሰግናለሁ! በፍጹም ቅንነት ላጎደልናቸው ነገሮችም ይቅርታ እጠይቃለሁ!” ብለዋል ኢንጂነር ታከለ፡፡
ኢንጂነር ታከለ አንዳሉት በከንቲባነት ያገለገሉባቸው ሁለት አመታት ወድ መሆናቸውንና ፈተናዎችን አልፈው ስኬት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
አዳዲስ ፕሮጀክቶችን መጀመርና መመረቅ የየእለት ስራቸው እንደነበረ የገለጹት ምክትል ከንቲባው በተገኙት ስኬቶችም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት ኢንጂነር ታከለን ጨምሮ ለ10 የፌደራል ባለስልጣናት ሹመት ሰጥተዋል፡፡