ፌደራል ፖሊስ መቀሌ የገባው በ2ኛው የናይሮቢ የሰላም ስምምነት መሠረት
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፌደራል ተቋማትን ለመጠበቅ መቀሌ ከተማ መግባቱ ተገለፀ።
ፌደራል ፖሊስ ወደ መቀሌ ከተማ የገባው በሀገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት በፌደራል መንግስት መንግስት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ እንሆነ ተገጿል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ገብቶ ሥራ መጀመሩን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል።
- የመከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ስራ በዚህ ሳምንት ይከናወናል- አምባሳደር ሬድዋን
- የሰላም ስምምነቱን የሚከታተለው የአፍሪካ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን መቀሌ ገባ
መንግስትና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የደረሱባቸውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የሚገኙ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሚተዳደሩ አየር ማረፊያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የባንክና ሌሎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የፌደራል ተቋማት አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከቀናት በፊት በትዊተር ገታቸው በሳፈሩት ጽሁፍ፤ በ2ኛው የናይሮቢ የሰላም ስምምነት መሠረት ህወሓት የታጠቃቸው ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን ለመንግስት የማስረከብ ስራ እስከ ሀሙስ እንደሚከናወን መግለጻው ይታወሳል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የታዛቢ ቡድን በሰላም ስምምነቱ የተጠቀሱ ነጥቦች ተፈጻሚነታቸውን ለማረጋገጥ በዛሬው እለት መቀሌ ገብተዋል።
በያዝነው ሳምንትም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግስ ልዑክ ወደ መቀሌ ማቅናቱም አይዘነጋም።