መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ሙሉበሙሉ ተቆጣጠረ-ጄነራል ብርሃኑ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመጨረሻ የህግ ማስከበር ዘመቻ እንዲያካሂድ በከትናንት በስትያ መታዘዙን ገልጸው ነበር
ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ “ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ” መቀሌ መግባት መቻሉን አስታውቀዋል
ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ “ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ” መቀሌ መግባት መቻሉን አስታውቀዋል
መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ መሙሉ መቆጣጠሩን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መከላከያ ሰራዊት በመጨረሻው “የህግ ማስከበር ዘመቻ” የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ወደ ሆነቸው መቀሌ መግባት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ፣ ከተሞቻችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት” እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ቡድን ጋር አለመሆኑን አረጋግጧል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የህወሓት ሀይል የጤና ተቋማትን፣ ተ/ቤቶችን፣ ድልድዮችን፣ መንገዶችን፣ መሥሪያ ቤቶችን አውድሟል ብለዋል፡፡
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለምግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥቅምት 24 ህወሓት በክልሉ በሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት መሰንዘሩንና በህወሓት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከሳወቁ በኋላ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በከትናንት በስትያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለውን “የህግ ማስከበር ዘመቻ” የመጨረሻ ምእራፍ እንዲያካሄድ መታዘዙን ማስታወቃቸው ይታሳል፡፡