የኢትየጵያ ሲቪል ማህበራት ህብረት ጥምረት 2500 የምርጫ ጣቢያዎችን መታዘቡን ገለጸ
ጥምረቱ 4000 የሚሆኑ ታዛቢዎች ለማሰማራት ማቀዱኑንና 3000 ገዳማ የሚሆኑ ያህል ማሰማራቱን አስታውቋል
ጥምረቱ በምርጫው እለት በምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር ያየውን ትዝብት በ2 ቀናት ውስጥ ይፋ ማድረጉንም ገልጿል
የኢትዮጵያ ሲቭል ማህበራት ህብረት ለምርጫ ጥምረት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታምራት ከበደ በዛሬው እለት እንዳስታወቁት ጥምረቱ 2400 የሚሆኑ ታዛቢዎችን በማሰማራት 2500 የምርጫ ጣቢያዎችን መታዘቡን አስታውቋል፡፡
አቶ ታምራት ይህን ያሉት ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ለማድረግ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
አቶ ታምራት ጥምረቱ በምርጫ ጣቢያዎች ከተዘዋወረ በኋላ የተመለከታቸውን ውስንነቶችንና መልካም ነገሮችን በሁለት ቀናት ውስጥ ሪፖርት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ ጥምረቱ 4000 የሚሆኑ አባላት ለማሰታማራት አቅዶ ወደ 3000 የሚሆኑ የማህበሩ አባላት ምርጫውን ታዝበዋል ብለዋል አቶ ታምራት፡፡
በኢትዮጵያ 6ኛ ዙር የተወካዮች ምክርቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ፤ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሰኔ 14፣2013 መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ምርጫው በ673 የምርጫ ጣቢያዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች እየተካሄደ ተካሂዷል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ አልተካሄደም፡፡ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 ለማካሄ አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ እንደማይካሄ አስታውቆ ነበር፡፡
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ጻግሜ 1 እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በምርጫ ከ38 ሚሊዮን ህዝብ ድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል፤45ሺ የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲሰማሩ ቦርዱ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡የምርጫ አጠቃላይ ጊዜያዊ ውጤት በተካሄደ በ10 ቀናት ውስጥ ይፋ የሚደረግ ቢሆንም የምርጫ ክልል ውጤቶች ወደ ማእከል ለመድረስ ጊዜ በመውሰዳቸው በፍጥነት ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን ቦርድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡