ብልፅግናን ጨምሮ 26 ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ
ፓርቲዎቹ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲያሰውቁትም ቦርዱ ጠይቋል
ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርጉ የተጠየቁት ፓርቲዎችም ሀገራዊ እና ክልላዊ መሆናቸው ተነግሯል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 ሀገራዊ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ አሳሰበ።
ቦርዱ ባወጣው መግለጫ፤ ከ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው አለማቅረባቸውን አስታውቋል።
ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑን ያስታወሰው ቦርዱ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው እለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማሳቱን ተከትሎ ፓርቲዎቹ ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ አሳስቧል።
በአንደ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ የሚያካሂዱት ፓርቲዎችም
ሀገራዊ ፓርቲዎች
1. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
2. የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ
3. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
4. ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
5. የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
6. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
7. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
8. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
9. ብልፅግና ፓርቲ
10. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ
11. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
12. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
13. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
ክልላዊ ፓርቲዎች
1. የሲዳማ አርነት ንቅናቄ
2. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
3. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. ኅዳሴ ፓርቲ
6. የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
7. የአፋር ሕዝቦች ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
8. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ
9. ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
10. ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ ሉዓላዊነት
11. የአርጎባ ብሔረ ሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
12. የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
13. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።