በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በውጊያው ኮሞቱ መካከል ኢትዮጵያዊን እንደሚገኙበት መረጃዎች እየደረሱኝ ነው ብሏል
በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ፤ “በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ኢትዮጵያዊን እንደሚገኙበት መረጃዎች እየደረሱን ነው” ብሏል።
ኤምባሲው በጦርነቱ የኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ቢገልጽም በቁጥር ግን አላስታወቀም።
ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።
በሱዳን ባሳለፍነው ቅዳሜ ጠዋት በሀገሪቱ መደበኛው የመከላከያ ሰራዊት እና “ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ)” ተብሎ የሚጠራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ለ4ኛ ቀን ቀጥሏል።
በጦርነቱ 200 ገደማ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ ከ1ሺህ 400 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም እየተነገረ ይገኛል።