አውሮፓ ለገጠመው የኃይል ቀውስ 800 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ አድርጓል ተባለ
ለኃይል ቀውሱ ሩሲያ ላይ ጥገኛ የሆነው የኃይል አቅርቦት መስተጓጎል ነው ተብሏል
270 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ በመመደብ ጀርመን በደረጃው ቀዳሚ ሆናለች
የአውሮፓ ሀገራት ዜጎችንና ኩባንያዎችን ከከፍተኛ የኃይል ወጭ ለመከላከል ወደ 800 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ አውጥተዋል ተብሏል።
ተመራማሪዎች የአዉሮፓ ህብረት ሀገራት አሁን 681 ቢሊዮን ዩሮ ለኃይል ቀውስ መድበዋል ያሉ ሲሆን፤ ብሪታንያ 103 ቢሊዮን ዩሮ እና ኖርዌይ ስምንት ቢሊዮን ዩሮ ከፈረንጆቹ መስከረም 2021 ጀምሮ አውጥተዋል ብለዋል።
ብሩጀል የተባለ የምርምር ተቋም የአውሮፓ ሀገራት በድምሩ 792 ቢሊየን ዩሮ ወጪ አድርገዋል። ይህም ተቋሙ ባለፈው ህዳር ይፋ ካደረገው 706 ቢሊዮን ዩሮ ግምገማው ጋር በማወዳደር ከሩሲያ የኃይል አቅርቦት መስተጓጎል እንደ ምክንያት ተጠቅሷል።
270 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ በመመደብ ጀርመን በደረጃው ቀዳሚ ሆናለች።
በነፍስ ወከፍ ሉክሰምበርግ፣ ዴንማርክ እና ጀርመን ከፍተኛ ወጪ ያወጡ ሀገራት ናቸው ተብሏል።
ሀገራቱ ለኃይል ቀውስ የመደቡት ወጪ የአውሮፓ ህብረት ለኮቪድ-19 ማገገሚያ ፈንድ ከመደበው 750 ቢሊዮን ዩሮ ጋር ተቀራራቢ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የምርምር ተቋሙ እንዳለው የመንግስታት አብዛኛው ድጋፍ ያተኮረው በነዳጅ የታክስ ቅነሳ ወይም የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጣሪያን ማስተካከል ላይ ነው።ሰፋ ያለ የገንዘብ ድጋፍን ለማስቀጠል ሀገራት በጀት ስለሚያንሳቸው አማራጮች ላይ ማተኮር አለባቸው ብሏል።