አረብ ኤምሬትስ “የዩክሬን ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚደረጉ ጥረቶችን እደግፋለሁ” አለች
ሩሲያን የጎበኙት የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳት የዩክሬን ቀውስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቋጭ ጠይቀዋል
የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማሲያው ውይይቶች እንዲካሄዱ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል
አረብ ኤምሬትስ የዩክሬን ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫው፤ የዩክሬን ቀውስ ዓለም አቀፍ ህግጋትን ባከበረ መልኩ በዲፖሊማሲያ መንገዶች እና በውይይት እንዲፈታ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።
በዩክሬን ውስጥ ባለው ቀውስ ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል
የሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሩስያ ጉብኝት "አረብ ኤሚሬትስ በቀጣናው እና በአለም ላይ ቀጣይነት ያለው ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ መሆኑን ም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳት በዛሬው ለት ይፋዊ የስራ ጉብኘት ለማድረግ ሩሲያ መግባታቸው ይታወቃል።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፤ ከዚህም የዩክሬን ቀውስ ጉዳይ አንዱ ነበረ።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የዩክሬን ቀውስ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቋጭ የጠየቁ ሲሆን፤ አረብ ኤምሬትስ በአለም ላይ የሰላም እና መረጋጋት መሰረትን ለማጠናከር የበኩሏን ጥረት እንድታደርግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እየታዩ ላሉ ቀውሶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት ሀገራው እንደመትሰራም ፕሬዝዳነቱ አረጋግጠዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው በገልፍ ቀጠና “ትልቅ” ሲሉ የጠሯትን አረብ ኤምሬትስ ችግሮችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ለምታሳየው አቋም አመስግነዋል።
ሩሲያ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር እያደረገች ያለው ግንኙነት እያገደ መሆኑን ያስታወቁት ፑቲን፤ይህም ለቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መረጋጋት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።