በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ማብቃቱን ተከትሎ ጦርነቱ ተባብሶ ቀጥሏል
በዛሬው እለት በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ካርቱም ፣ በባህሪ እና በሰሜናዊ ብሉ ናይል ጦርነት እየተካሄደ ነው ተብሏል
ከተጀመረ ሰባት ሳምንታትን ያስቆጠረው ጦርነት 400ሺ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል
የሱዳን ተፋላሚዎች በሳኡዲ አረቢያ እና አሜሪካ አማካኝነት የደረሱት የተኩስ አቁም ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ በካርቱም በበርካታ ቦታዎች ግጭቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ነዎሪዎች ተናግረዋል።
በናይል መገናኛ ላይ ከሚገኙት ከተሞች አንዷ በሆነችው ኦምዱርማን አውሮኘላን መከስከሱን እማኞችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በአየር እያጠቃ ያለው የሱዳን ጦር ስለአውሮኘላኑ መከስከስ ያለው ነገር የለም።
ምንም እንኳን ተኩስ አቀሙን ለማራዘም የተጀመረው ንግግር ባለፈው ሳምንት ቢቋረጦም፣ ሳኡዲ አረቢያ እና አሜሪካ በጅዳ ከሚገኙበት የተፋላሚ ኃይሎች ልኡካን ጋር በየቀኑ እየተወያዩ ነው።
ወይይቶቹ በድጋሚ እከሚጀመሩ ድረስ የሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ ላይ ያተከረ መሆኑን ሁለቱ ሀገራት ባወጡት መግለጫ አስታወቀዋል።
በፈረንጆቹ ግንቦት 22 የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ያበቃው ትናንት ምሽት ላይ ነው። ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፋላሚ ኃይሎቹ ቀደም ሲል እንደረሷቸው ስምምነቶች ሁሉ ቢጣስም፣ የግጭቱን መጠን መቀነስ ችሎ ነበር።
በዛሬው እለት በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ካርቱም ፣ በባህሪ እና በሰሜናዊ ብሉ ናይል ጦርነት እየተካሄደ ነው ተብሏል።
ከተጀመረ ሰባት ሳምንታትን ያስቆጠረው ጦርነት 400ሺ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።