የጋምቤላ ከተማ በ ”ሸኔ እና በጋምቤላ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ” ነበር ተባለ
የጋምቤላ ከተማ አሁን ላይ በከፊል ነጻ መውጣቱ ተገልጿል
ዛሬ በከተማው ከማለዳ ጀምሮ ከባድ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ተነግሯል
የጋምቤላ ከተማ በ ”ሸኔ እና በጋምቤላ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ” ነበር ተባለ፡፡
ታጣቂዎች,ቹ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ በጋራ ተኩስ ከፍተው እንደነበር የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡
የከተማው ነዋሪ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ሀይሉ እያደረገ ላለው የህግ ማስከበር ተግባር የበኩሉን እንዲወጣም ክልሉ ጠይቋል።
የከተማው ነዋሪዎች ሁኔታውን በተመለከተ ለአል ዐይን እንዳሉት መንግስት ”ሸኔ” በሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው የታጠቀ ኃይል እንዲሁም በ“ጋምቤላ ነፃነት ግንባር” ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር፡፡ ሆኖም አሁን ላይ ከተማውን በድንገተኛ የተኩስ እርምታ ያወኩት ታጣቂዎች አሁን ላይ ታጣቂዎች በመንግስት ኃይሎች ተከበዋል እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፡፡
አል ዐይን አማርኛ ለክልሉ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ውገቱ አዲንግ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም አሁን መመለስ እንደማይችሉ ነገር ግን ከሰዓት በኋላ ምላሽ እንደሚሰጡበት በመግለጽ ለጊዜው ለጥያቄው ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡
ሆኖም የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በይፋዊ የፌስቡክ የማህበረሰብ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሆነ ተከፍቶ የነበረው ተኩስ ባይቆምም አሁን ላይ መጠነኛ መረጋጋት አሳይቷል፡፡
በድንገት ማለዳ ላይ ከተማዋን በእሩምታ ያናወጠው የተኩስ ልውውጥ ከንጋቱ 12 ሰዓት 30 የጀመረ ሲሆን ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ዘልቋል፡፡ ሆኖም አሁኑ ላይ በከተማው መጠነኛ መረጋጋት እንደሚታይ ነገር ግን የተኩስ ልውውጡ አሁንም አልፎ አልፎም ቢሆን እንዳለ ነው የአል ዐይን የመረጃ ምንጮች የገለጹት፡፡
የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ከተማው በከፊል ነጻ ማውጣት ችለዋል የተባለ ሲሆን በሁለቱም ወገኖች በኩል ጉዳት መድረሱም ተገልጿል፡፡ሆኖም የጉዳቱ መጠን በውል ተለይቶ አልታወቀም፡፡