ከብሪታያው ብሌንሄም ቤተ መንግስት የተሰረቀው የወርቅ መጸዳጃ ቤት እቃ የት ገባ?
የመጸዳጃ ቤት አቃው የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችል ይጠቀሙበት የነበረ ነው

በአምስት ደቂቃ ውስጥ የተሰረቀው ይህ ውድ እቃ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አለው ተብሏል
ከብሪታያው ብሌንሄም ቤተ መንግስት የተሰረቀው የወርቅ መጸዳጃ ቤት እቃ የት ገባ?
ብሪታንያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በመምራ የሚታወቁት ዊንስተን ቸርችል ይጠቀሙበት የነበረው እና ከወርቅ የተሰራው የመጸዳጃ ቤት አቃ በሌቦች ተሰርቋል፡፡
ከአምስት ዓመት በፊት የተሰረቀው ይህ ውድ እቃ በየሶስት ደቂቃው በጎብኚዎች ይጎበኝ የነበረ ቢሆንም በአምስት ደቂቃ ውስጥ ደብዛው ጠፍቷል፡፡
ይህ የመጸዳጃ ቤት እቃ 18 ካራት ወርቅ ነው የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ዋጋም እንዳለው በወቅቱ ተገልጿል፡፡
የወርቅ መጸዳጃው የሚገኝበት ብሌንሄም ቤተ መንግስት በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን በየዓመቱ በአማካኝ በአንድ ሚሊዮን ጎብኚዎች ይጎበኛል፡፡
የዚህ ቤተ መንግስት ድምቀት የነበረው ይህ መጸዳጃ ቤት እቃ የሰረቀውን አካል የብሪታንያ ፖሊስ ክትትሉን ቀጥሏል የተባለ ሲሆን እስካሁን ሶት ተጠርጣሪዎችን ማሰሩ ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ጎብኚ መስሎ የገባ፣ እቃውን ያጓጓዘ እና የገዛ ነው የተባሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የሀገሪቱ ጠበቆች ወርቁ ተቆራርጦ እንደተሸጠ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ጠበቆች ተጠርጣሪዎቹ ያደረጓቸውን የመረጃ ልውውጦች፣ የሲሲቲቭ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እና ሌሎች ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡
ይሁንና የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አለማሳለፉ ተገልጿል፡፡
98 ኪሎ ግራም ይመዝናል የተባለው ይህ ወርቅ ስሪት መጸዳጃ ቤት በፍጥነት መሰረቁ እና ፖሊስ ንብረቱን ማስመለስ አለመቻሉ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡