አዲሱ መደበኛ ስብሰባውን ባደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተወሰነ ነው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2015 ዓ.ም በጀት 786 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ፡፡
ምክር ቤቱ በ2015 ዓ/ም የፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ለመደበኛ ወጪ ብር 347 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ ደግሞ 218 ነጥብ 11 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209 ነጥብ 38 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ብር በጀት እንዲያዝ ወስኗል ምክር ቤቱ፡፡
አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ 2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ሆኖ መቅረቡ ተገልጿል፡፡
በጀቱ ከ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የብር 111 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር ወይም የ16 ነጥብ 59 በመቶ እድገት አለው፡፡
ምክር ቤቱ የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አጽድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
የ 2014 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት 561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡