ገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ለፓርላማ ሊያቀርብ ነው
አቶ አህመድ ሽዴ ተጨማሪ በጀቱ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳውን የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ለመደጎም እንደሚውል ተናግረዋል
የተጨማሪ በጀት ጥያቄው ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡ ተገልጿል
የገንዘብ ሚኒስቴር፤ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እና ዜጎች ለማቋቋም የሚውል አዲስ በጀት ሊያጸድቅ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተዘጋጀው “የአዲስ ወግ” መርሃ ግብር ላይ መስሪያ ቤታቸው በጦርነት ምክንያት የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለማካካስ ብሎም መልሶ ለመገንባት ተጨማሪ በጀት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
የሚያስፈልገው ገንዘብ በሚኒስቴሩ በኩል ተሰርቶ ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡንም ነው አቶ አህመድ ያስታወቁት፡፡
በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ገልጸዋል፤ ከጸደቀ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትሩ፡፡
አቶ አህመድ “ባለፉት ወራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት ቢደርስብንም፤ ማክሮ ኢኮኖሚያችን በከፍተኛ ሁኔታ አልተዛባም። የውጪ ግብይትና መደበኛ ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ ተከውነዋል። ከሥራ ፈጠራ አንጻር በርካታ ዕድሎች አሉ። በጦርነቱ መካከል የመንግሥት መዋቅሮች መደበኛ አገልግሎታቸውን በአብዛኛው የሀገራችን ክፍል ቀጥለዋል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
“ከሽንፈት አመድ ውስጥ ሳይሆን፤ የአሸናፊነትን አቧራ አራግፎ የሚነሳ የማገገሚያ ዕቅድ ያስፈልገናል”- ፕ/ር መንግስቱ
የዕለት ደራሽ ዕርዳታ፣ ነጻ በሆኑ አካባቢዎች የመሠረተ ልማት መልሶ ግንባታ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲገቡ የማድረግ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን በማከልም “የደረሰውን ጉዳት አጥንቶ መልሶ የማቋቋም በጀት መድቦ መሥራት ቀጣዩ ርምጃ ነው፤ የልማት አጋሮች፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዚህ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል” አቶ አሕመድ ሽዴ፡፡
መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር ባለው ትብብር መሰረት ከዓለም ባንክ ጋር የ400 ሚሊዮን ዶላር የመልሶ ግንባታ ፕሮግራም የመቅረጽ ስራን በፍጥነት እያከናወነ መሆኑን ያነሱት አቶ አሕመድ፤ በብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩልም የ 350 ሚሊዮን ዶላር ፕሮግራም በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መንግስት ሌሎች የልማት አጋዦችን በማቀናጀት የሕብረተሰቡን አሴት በጋራ እንዲገነባ ያደርጋልም ብለዋል አቶ አህመድ፡፡
በተመድ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ስብሰባ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ካደረጉ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ውይይት መጀመሩን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለጸ
አሁን ላይ ከገቢ አንጻር መቀዛቀዝ ቢኖርም የውጭ ንግድ አፈጻጸሙ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያሉም ሲሆን የኢኮኖሚው ችግሩን ተቋቁሞ የማለፍ አቅም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ጦርነት ከተካሄደባው አካባቢዎች ውጭ ያሉ ሌሎች አካባቢዎች ላይ መደበኛ ስራዎች ሲካሄዱ መቆየታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በተለይ በግብርና መስክ በብዙ ቦታዎች መልካም ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡