መንግስት የአዋጁን ተፈጻሚኒት ማሳጠር ያስፈለገው አሁን “ስጋቱን በመደበኛ የህግ ማስከበር ስራ መከላከል ስለሚቻል” ነው ብሏል
የኢትየጵያ መንግስት ህወሃት በሀገር ህልውና ሉአላዊነት ላይ ደቅኖታል ያለውም ስጋት ለመቀልስ ጥቅምት 24፣2014 የጣለውን ለስድስት ወራት የሚቆይ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር፡፡
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባ አዋጁ ጊዜው ሳይደር ቀደም ብሎ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ም/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፤ መንግስት በሽብር የጠረጠረውን ማንኛውንም ሰው በቁጥጥር ስር እንደሚያደርግ አስታወቀ
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርሆዎችን ባከበረ መልኩ እየተተገበረ አይደለም - ኢሰመኮ
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያለአግባብ የተጠቀሙ 4 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተከሰሱ
መግለጫው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት “አስፈላጊ የነበረበት ሁኔታ አሁን ላይ ስለተቀየረ እና ስጋቱን በመደበኛ የህግ ማስከበር ስራ መከላከል ስለሚቻል” ለስደስት ወራት የታወጀውን አዋጅ ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡
የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲያጸድቀው መተላለፉንም መግለጫው ጠቅሷል፡፡
አዋጁን የሚያስፈጽም “የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ዕዝ” በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ስር እንደሚሆን ተገልፆ ነበር፡፡ ይህ ዕዝም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ (ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ) እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ዕዙ የሀገሪቱን ሁሉንም የጸጥታ አካላት ማዘዝና ማንቀሳቀስ እንደሚችል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የተቋቋመው ዕዝ ማንኛውንም መሳሪያ የታጠቀ አካልን የማዘዝና የማሰማራት ስልጣን እንደተሰጠው ጌዲዎን ጢሞቲዮስ ተናግረዋል፡፡
ህወሃት የደቀነውን ስጋት ለመቀልበስ፣የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ዕዝ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ግዳጅ እንዲሰማሩ፤ መሰማራት የማይችሉ መሰማራት ለሚፈልጉ መሳሪያቸውን እንዲሰጡ የማድረግ፤የመገናኛ ዘዴዎችንና የትራንስፖርት አገልግሎትን የመዝጋት ስልጣን ነበረው፡፡
አዋጁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመታቸውን አሳወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ግንባር ከዘመቱ በኃላ ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት የምስራቅ አማራና አፋር ክልል እንዲወጣ ማድረግ መቻሉን መንግስት ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ነገርግን ህወሓት አማራነ አፋር የወጣሁት ለሰላም እድል ለመስጠት ሲል ተደምጧል፡፡
ጥቅምት 24፤2014 አንድ አመት ያስቆጠረው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ አሜሪካና የአፍሪካ ህብርት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን እየገለጹ ነው፡፡