ስፖርት
የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አግኝተው የማያውቁ 10 ሀገራት
ኦሎምፒክ ውድድር ከተጀመረ 128 ዓመት ቢያስቆጥርም በርካታ የዓለማችን ሀገራት ከተሳትፎ የዘለለ ሚና የላቸውም
ቡርኪናፋሶ ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት በታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች
በፈረንጆቹ 1896 በግሪክ የተጀመረው የኦሎምፒክ ውድድር በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው በፓሪስ ከተማ ከነገ በስቲያ ይጀመራል፡፡
206 ሀገራት በሚሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶችም እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ባለፉት 128 ዓመታት ውስጥ አንድም ሜዳሊያ ያላገኙ ሀገራት ያሉ ሲሆን አንጎላ፣ ማሊ እና ባንግላዲሽ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ውድድር የተካፈለችው በጎርጎሮሲያውያን ዘመን አቆጣጠር በ1956 ሲሆን በ1960 በተካሄደው ሮም ኦሎምፒክ አበበ ቢቂላ አማካኝነት በማራቶን ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡