ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - አንድ ተማሪ “የተፈጥሮ ሞት“ አጋጠመው
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - አንድ ተማሪ “የተፈጥሮ ሞት“ አጋጠመው
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወንዶገነት አንድ የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጂ ተማሪ በትናንትናው እለት 11 ሰአት አካባቢ ዶርሙ ውስጥ በመታመሙ፣ በተማሪዎች እርዳታ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ጸ/ቤት ኃለፊ አቶ አየለ አዳቶ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡
አቶ አየለ እንዳሉት ተማሪው ሆስፒታል ከገባ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡
የሞቱን ምክንያት ለማወቅና ለተጨማሪ ምርመራ አስከሬኑ ወደ አዲስ አበባ ሚኒልክ ሆስፒታል መላኩን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ተማሪው በተፈጥሮ ምክንያት ነው የሞተው፤ ከዚህ ውጭ ግን የሚሰራጨው ወሬ ትክክል አይደለም፤ዩኒቨርሲቲውም ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያካሄደ ነው ብለዋል አቶ አየለ፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ዘርን መሰረት በሚያደርጉ ግጭቶች ተማሪዎች ለሞትና ትምህርታቸውን አ እንዲያቋርጡ ለሚያስገድዱ ችግሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡