ሩሲያ በዩክሬኗ የወደብ ከተማ ኦዴሳ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በዩኔስኮ በቅርስነት በተመዘገበ ህንጻ ላይ ጉዳት አደረሰ
በ19ኛው ክለፍዘመን የተገነባው ቅንጡ ሆቴል የእንግዳ መቀበያው እና ሌሎች ክፍሎቹ ወደ በፍርስራሽነት መቀየራቸው ተዘግቧል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ጥቃቱ ሆነ ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን እና የዩክሬንን የአየር መካላከያ ሰርአታ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግረዋል
ሩሲያ በዩክሬኗ የወደብ ከተማ ኦዴሳ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በዩኔስኮ በቅርስነት በተመዘገበ ህንጻ ላይ ጉዳት አደረሰ።
የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬኗ የወደብ ከተማ ኦደሳ ማዕከል ላይ የፈጸሙት ጥቃት በዩኔስኮ በቅርስነት በመተዘገባ ህንጻ ላይ ጉዳት ማድረሱና ሰባት ሰዎት ማቁሰሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጥቃቱ ሆነ ተብሎ የተፈጸመ መሆኑን እና የዩክሬንን የአየር መካላከያ ሰርአታ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግረዋል።
የኖርዌይ ዲፕሎማቶች ጥቃቱ በተፈጸመበት ታሪካዊ ቦታ አካባቢ ከነበሩት ሰዎች መካከል ነበሩ ብለዋል ዘለንስኪ።
የኦደሳ ግዛት አስተዳዳሪ ኦሌክ ኪፐር በጥቃቱ ሰባት ሰዎች መጎዳታቸውንና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ቦታው እንዳሉ ገልጸዋል።
በ19ኛው ክለፍዘመን የተገነባው ቅንጡ ሆቴል የእንግዳ መቀበያው እና ሌሎች ክፍሎቹ ወደ በፍርስራሽነት መቀየራቸውን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መውጣታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከሆቴሉ በተጨማሪ ሙዚየሙን ጨምሮ ሌሎች ህንጻዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
ኪፐር ለሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በተከታታይ ሶስት ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።
ዘለንስኪ እንደገለጹት ጥቃቱ "በከተማዋና በህንጻዎች ላይ በቀጥታ የተቃጣ ነው"ብለዋል።
"የአየር መካከል ስርአት ዋና ትኩረታችን ነው። ለሀገራችን የተሻለ ጥበቃ ለማድረግ ከሁሉም አጋሮቻችን ጋር እየሰራን ነው።"
ዘለንስኪ ከዩክሬን የጦር አዛዦች ጋር ባደረጉት ስብሰባ መሳሪያዎችን ማሻሻልና ፈጥኖ በማቅረብ ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
ከሶስት አመት በላይ ያስቆጠረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የቀጠለ ሲሆን ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን በርካታ የዩክሬን መንደሮችን በተከታታይ እየተቆጣጠረች ትገኛለች።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ጦርነቱን ማስቅም የሚያስችል እቅድ እንዳላቸውና ይህንኑ እውን ለማድረግ ከሩሲያው መሪ ከፑቲን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።ፑቲንም ንግግር ለማድረግ ያላቸውን ፈቃደኝነት ገልጸዋል።