የፌደራል መንግስቱ ደግም ህወሓት ከሽብር የሚነሳበትን መንገድ እንዲያመቻች ተስማምቶ ነበር
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በህወሓት ላይ አስተላልፎት የነበረውን የሽብርተኝነት ፍረጃ ማንሳቱን አስታውቋል።
በም/ቤቱ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ 60 ድምጽ ተቃውም እና በ5 ድምጽ ተአቅቦ ሲስተዋል በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን ም/ቤቱ ገልጿል።
ህወሓት፣ በፌደራል መንግስቱ አቅራቢነት በም/ቤቱ በሽብር እንዲፈረጅ የተደረገው በፌደራል መንግስቱና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ጦርነት ካመራ ከወራት በኋላ ነበር።
መንግስት ህወሓት በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ያደረገው "ሀገረ መንግስቱን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር" ተሳትፏል በሚል ነበር።
ሁለት አመታት ያስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የፌደራል መንግስትና ህወሓት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፣ፕሪቶሪያ የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት በማድረጋቸው መቆሙ ይታወሳል።
በስምምነቱ መሰረት ህወሓት ትጥቅ መፍታትን ጨምሮ ሌሎች ግዴታዎችን እንዲወጣ ሲስማማ፣ የፌደራል መንግስቱ ደግም ህወሓት ከሽብር የሚነሳበትን መንገድ እንዲያመቻች ተስማምቶ ነበር።