ም/ቤቱ ለምክክር ኮሚሽን ከተጠቆሙት እጩ ኮሚሽነሮች መካከል 42ቱን መለየቱን ገለጸ
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጥቆማ ላለፉት ሳምንታት ሲካሄድ ነበር
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ 632 ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበሉን አስታውቋል
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 42ቱን መለየቱን የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡
ም/ቤቱ ለተቋቋመው የምክክር ኮሚሽን የሚሆን እጩዎች ጥቆማ እንዲደረግ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
ም/ቤቱ ባወጣው መግለጫ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ለአንድ ሳምንት መራዙን እጩዎችን ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ሲቀበል መቆየቱን ገልጿል፡፡
ከመላ ሀገሪቱ 632 እጩ ኮሚሽነሮች በጥቆማ መቅረባቸውን ም/ቱ አስታውቋል፡፡
አዋጁ ለአፈ-ጉባኤውና ለአፈ-ጉባኤው ጽ/ቤት በሰጠው ስልጣን እንዲሁም በአዋጁ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ከቀረቡት 632 ዕጩዎች መካከል 42ቱ መለየታቸውን ክቡር አፈ-ጉባኤው ተናግረዋል፡፡
አክለውም በቀረቡት 42 ዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር እየተደረገበት ነው ብሏል ም/ቤቱ፡፡
ም/ቤቱ በመግለጫው” በቀጣይ ሳምንትም የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራር አካላት በሚገኙበት በዕጩዎች የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ላይ ምክክር” ይደረጋል ብሏል፡፡
ም/ቤቱ በጽረ-ገጽና በማህበራዊ ሚዲያ የእጩዎችን ማንነት ከጸገለጸና አስተያያት ከተሰበሰበ በኋላ 11ዱ ኮሚሽነሮች ለም/ቤት ቀርቦ ይጸድቃል ብሏል፡፡